የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ቁርሾ እየተዘጋ ይመስላል፡፡ ያኔ በተቃራኒ ጎራ ተሰልፈው የተናነቁት የዩናይትድ ስቴትስና ጃፓን ዛሬ ወዳጆች ናቸው፡፡ የእርቅን ጉዳይ ግን ሁለቱም ዝም ዝም ከማለት በስተቀር ጨርሶ አልዘነጉትም ነበር፡፡
የተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዚዳንታዊ ድል ፖለቲካውን ቀየረው፡፡
በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ እጁን በሚያስገባ በሩስያም ሆነ በማንኛውም የውጭ አገር መንግሥት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አስጠነቀቁ።
የዩናይትድ ስቴትሱ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእሥራኤል ቀጣዩን የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር መረጡ፡፡
ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቴክሣሱን የነዳጅ ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ ለአስተዳደራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት መርጠዋል፡፡
በዩናይትድ ስቴትስ ኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሶማሊያዊ ስደተኛ በሚያሽከረክረው መኪና ሰዎችን በመግጨትና በስለት በመውጋት ጉዳት ማደርሱን ተከትሎ የአካባቢው ማኅበረሰብ ተማሪው ይህን ጥቃት ለማድረስ ምን እንደገፋፋው ለመረዳት አዳግቶት ቆይቷል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ካቢኔአቸውን እያዋቀሩ ባሉበት በዚህ ወቅት አሜሪካዊያንም ዓለምም እነማንን እያነሱ ለየጉዳዩ አውራ እንደሚያደርጉ በንቃት እየተከታተሉ ነው፡፡
ቃለመሐላ ፈፅመው በትረ መንግሥቱን ሊረከቡ ከስድስት ሣምንታት ብዙም ያልበለጠ ጊዜ በቀረበት በአሁኑ ወቅት፣ ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የካቢኔ አባሎቻቸውን ለማሟላት በጥድፊያ ላይ መሆናቸው ተሰማ።
የዩናይትድ ስቴትስሱ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ፣ በዛሬው ዕለት አስተዳደራቸው ሽብርተኛነትን በመዋጋት እረገድ ያደረገውን አስተዋጽዖ በማወደስ ተናገሩ።
ተመራጩ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ሥራ በይፋ ሲጀምሩ ቅድሚያ የሚሰጧቸው ተግባራት ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ ስትከተለው የቆየችው ፖሊሲ ሊቀየር እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ይገምታሉ።
የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ሣምንት ውስጥ ቀሪ የካቢኔ አባሎቻቸውን እንደሚያሳውቁ ገልፀዋል፡፡
በዩናይትድ ስቴትስ በተካሄደ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሽንፈት የደረሰባቸው ዲሞክራቶች የወደፊት አካሄዳቸውን እየመረመሩና እርምጃም እየወሰዱ ነው።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ለሃያ አንድ ሰዎች ፕሬዚደንታዊ የነፃነት ሜዳልያ ሸለሙ።
ከፓሲፊክ አቋራጭ አጋርነት ስምምነት ለመውጣት ደብዳቤ መፃፍ ሥራ የሚጀምሩበት የመጀመሪያ ቀን ሥራቸው ከሆኑት ተግባራት መካከል አንዱ እንደሚሆን ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በአውሮፓ የጀመሩትን የመጨረሻ የውጭ ሀገራት ጉብኝት በፔሩ አጠናቀውታል።
በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ያለፉት ጥቂት ቀናት በተመራጩ ፕሬዚዳንት የሽግግር አካሄድ ላይ ትኩረት ባደረጉ እንቅስቃሴዎች የተመሉ ሆነው አልፈዋል።
የተመራጩን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የዶናልድ ትራምፕን የሽግግር ዝርዝር በሚያወሳው ድረ-ገፅ መሠረት ሚስተር ትራምፕ የካንሳሱን የምክር ቤት አባል ማይክ ፖምፒዮን የሲአይኤ ኃላፊ አድርገው ሰይመዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ሁሉን አቀፍ የሆነ የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ ድጋፍ መርኃግብር አውጥታ ከአፍሪካ ሃገሮች ጋር ስትሠራ ቆይታለች፡፡
ተመራጩ ፕሬዚዳንት ሁለት ወሣኝ ነገሮችን እንደምን እንደሚያቻችሉ ፈተና ይሆንባቸዋል እየተባለ ነው።
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በአውሮፓና በደቡብ አሜሪካ በሚያደርጉት ጉዞ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኔቶን ጨምሮ ከመላው ዓለም መሪዎች ጋር ግንኙነታቸውን ለመቀጠል እንደሚሹ መልዕክት መያዛቸውን ገለፁ።
በዩናይትድ ስቴትስ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአስተዳደራቸው ውስጥ የሚካተቱትን ባለሥልጣናት ለመለየት እየሠሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የቀድሞው የኒውዮርክ ከተማ ከንቲባ ሩዲ ጊሌአኒ ቀጣዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለመሆን ቀዳሚ ዕጩ መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት የሆኑት ሪፐብሊካዊው ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት ከነበራቸው የጠነከረና የከረረ አነጋገር ሰሞኑን ለስለስ ብለው ታይተዋል፡፡
የዶናልድ ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንትነት መመረጥ በአጠቃላይ በአፍሪካ በተለይም ደግሞ በኢትዮጵያ ላይ ሊኖረው ስለሚችለው አንድምታ እንዲተነትኑልን የአፍሪካ ጉዳዮች ተመራማሪ የሆኑትን ዶ/ር አየለ በከሬን ጋብዘናል፡፡
አፍሪካ በዩናይትድ ስቴትስ እየተካሄደ ባለው ሠላማዊ የሥልጣን ሽግግር ብዙ መማር እንዳለባት ኢትዮጵያውያን አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የፕሬዚዳንትነት ሥልጣናቸው ከማብቃቱ በፊት የመጨረሻ የውጭ ሃገራት ጉብኘት ለማካሄድ ዛሬ ይጓዛሉ።
ተጨማሪ ይጫኑ