በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለአካባቢ ጥበቃ ትራምፕ ሰው ሾሙ


የኦክላሆማ ጠቅላይ ግዛት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ስካት ፕሩዪት
የኦክላሆማ ጠቅላይ ግዛት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ስካት ፕሩዪት

የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ካቢኔአቸውን እያዋቀሩ ባሉበት በዚህ ወቅት አሜሪካዊያንም ዓለምም እነማንን እያነሱ ለየጉዳዩ አውራ እንደሚያደርጉ በንቃት እየተከታተሉ ነው፡፡

የአሜሪካዊያን የውስጥ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የዓለምም ሥጋትና ትኩረት ከሆኑት ጉዳዮች መካከል የዓለማችን የአየር ንብረት መለዋወጥ፣ የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃና የዓለማችን ግለት በእውኑ እጅግ አንገብጋቢ ናቸው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ

​የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እየሰጧቸው ካሉ የሰሞኑ ሹመቶች መካከል ለሃገራቸው የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ ድርጅት አለቃነት የሰየሟቸው የኦክላሆማ ጠቅላይ ግዛት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ስካት ፕሩዪት “የአየር ንብረት ለውጥ የለም” ብለው ከሚያምኑ አሜሪካዊያን አንዱና እንዲያውም ተሟጋችም ናቸው፡፡

ይህ የሚስተር ትራምፕ ሹመት ዛሬ ብዙዎችን እያነጋገረና እየፈተነ ያለ ውሣኔ ነው፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ለአካባቢ ጥበቃ ትራምፕ ሰው ሾሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:56 0:00

XS
SM
MD
LG