ይህ መርኃግብር የአፍሪካ ሃገሮች የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና ለመለማመድ እንዲችሉ የሚያግዝ ነው፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ እአአ ከ2010 እስከ 2015 ዓ.ም ባሉት አምስት ዓመታት የ3.3 ቢሊየን ዶላር የአባባቢ ጥበቃ ድጋፍ እርዳታ ሰጥታ ሃገሮች አካባቢ በካይ የሆኑ ምርቶችን ከማውጣት እንዲገቱና የአየር ንብረት ለውጡን መቋቋም የሚችል ተለማጭ አቅም እንዲፈጥሩ ለማድረግ አግዛለች፡፡
ከሠሃራ በስተደቡብ ያሉ ሃገሮች የኤሌክትሪክ ኃይልን በስፋት ማምረትና ማዳረስ እንዲችሉ ለማገዝ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ለዘረጋው “ፓወር አፍሪካ ኢንሼቲቭ” ለሚባለው መርኃግብር ማስፈፀሚያ የመደበው የሰባት ብሊዮን ዶላር ድጋፍ ከግሉና ከመንግሥት ምንጮች ተጨማሪ 52 ቢሊዮን ዶላር ለ
ማሰባሰብ አቅም ሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በካይ የሆኑ ጋዞችን ወደ ከባቢ አየር መልቀቅን ለመቀነስ የገቡትን ቃል እያከበሩ አይደሉም በተባሉ በኢንዱስትሪ ልማት የተራመዱ የቡድን ሃያ ሃገሮች ላይ ወቀሣ እየተሰማ ነው፡፡
ሃገሮቹ ሙቀት አማቂ የሆኑ ጋዞችን ማውጣት ለመቀነስ የተስማሙት ፓሪስ ላይ በወጣውና በተፈረመው ውል መሠረት ነው፡፡
ይሁን እንጂ የዩናይትድ ስቴትሱ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምረጡኝ ዘመቻቸው ወቅት አደርገዋለሁ ያሉትን ሁሉ የሚያደርጉ ከሆነ እስከአሁን የተጨበጠው ሁሉ አደጋ ሊገጥመው፤ በሃገሮች ዘንድ የሚታየው ዝግጁነት ሊቀዛቀዝ ይችላል የሚል ሥጋት አላቸው፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ከፓሪስ ውል እንደሚወጡ ዝተዋል፡፡ የከርሰ-ምድር ዘይትና የድንጋይ ከሠልን የመሣሰሉ የአካባቢ በካይነታቸው የተረጋገጠ የኃይል ምንጭ የሆኑ ምርቶችን እንደሚያጠናክሩ፣ የተዘጉትን እንደሚከፍቱና አዳዲስ የልማትና የብዝበዛ ፕሮጀክቶችን እንደሚዘረጉ ተናግረዋል፡፡
ለመሆኑ ዶናልድ ትራምፕ ያሉትን ሁሉ ያደርጉ ይሆን; ካደረጉስ መዘዙ ምን ይሆናል;
በካናዳው ዩኒቨርሲቲ ኦቭ ካልጋሪ ተባባሪ ፕሮፎሰር፤ የአየር ንብረት ጉዳይ ተመራማሪና ዓለምአቀፍ ተሟጋች የሆኑት ዶ/ር ጌታቸው አሰፋ መልስ አላቸው፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡