በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የካቢኔ አባላቶቻቸው


ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ
ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ

ቃለመሐላ ፈፅመው በትረ መንግሥቱን ሊረከቡ ከስድስት ሣምንታት ብዙም ያልበለጠ ጊዜ በቀረበት በአሁኑ ወቅት፣ ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የካቢኔ አባሎቻቸውን ለማሟላት በጥድፊያ ላይ መሆናቸው ተሰማ።

በዚህ ሣምንት የመከላከያው፣ የአካባቢ አየር ጥበቃው፣ የአገር ደኅንነቱን፣ የሥራና ከተማ ልማት መ/ቤቶች ኃላፊዎቻቸውን እንዲሁም በቻይና የዩናይትድ ስቴትስን አምባሳደር ይፋ እንዳደረጉ፣ የሽግግር ባለሥልጣኖቻቸው አስታውቀዋል።

በከርሠ ምድር የነዳጅ ውጤቶች ወይም ግብዓቶች ደጋፊነታቸው የሚታወቁት ስካት ፕሩቲ የኦክላሆማ ግዛት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ናቸው፤ የአካባቢ አየር ጥበቃ መሥሪያ ቤትን ይመራሉ ተብሎም ይጠበቃል።

ምንም እንኳን የሰዎች እንቅስቃሴ ለአየር ንብረት ለውጥ አስተዋጽዖ እንዳለው በሳይንስ የታመነ ቢሆንም፣ ፕሩቲ ግን በግሎባል ዋርሚንግ/በዓለም ግለት/ ተግባራዊነት ላይ በአላቸው አቋም ይተቻሉ።

በዚህም በፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ህጋዊ ዘመቻ ከፍተው እንደነበር ይታወቃል።

“የእኒህ ሰው መመረጥ አወዛጋቢ ነው” በማለት ብዙዎች ይከራከራሉ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የካቢኔ አባላቶቻቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:47 0:00

XS
SM
MD
LG