የዩናይትድ ስቴትሱ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደ ሌሎቹ ምርጫዎቻቸ ሁሉ፣ እኒህኛውም አወዛጋቢ ናቸው ተባለ።
የባንክራፕሲ/የንግድ ክስረት/ ተከራካሪ ጠበቃ የሆትን ዴቪድ ፍሬድማንን ነው፣ ዶናልድ ትራምፕ ለእሥራኤል አምባሳደርነት ያጩት።
ፍሬድማን ከምርጫው በኋላ ባደረጉት ንግግር እሥራኤል ዋና ከተማ ኢየሩሳሌም ውስጥ ባለው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ሥራቸውን ለመቀጠል ፈቃደኛ እንደሆኑ ገልፀዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የሚገኘው ቴልአቪቭ ነው። ፍልስጥኤማውያንም ሆኑ እስሥራኤላውያን ግን፣ ዋና ከተማችን ኢሩሳሌም ነው እንደሚሉና ይህም፣ የሰላም ድርድሩ አካል ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።
በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት የዶናልድ ትራምፕ አማካሪ የነበሩት ፍሬድማን የዩናይትድ ስቴትስን ኤምበሲ ከቴልአቪቭ ወደ ኢየሩሳሌም አዛውራለሁ ሲሉ ይህ ደግሞ፣ በተለይም ከአረቡ ዓለም፣ ቀላል ያልሆነ ዓለማቀፍ ተቃውሞ እንደሚገጥመው ይታመናል።