በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ኦባማ ለሲቪሎች ታላቅ የክብር ኒሻን ሸለሙ


ፕሬዚዳንት ኦባማ ለሲቪሎች ታላቅ የክብር ኒሻን ሲሰጡ
ፕሬዚዳንት ኦባማ ለሲቪሎች ታላቅ የክብር ኒሻን ሲሰጡ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ለሃያ አንድ ሰዎች ፕሬዚደንታዊ የነፃነት ሜዳልያ ሸለሙ።

ሚስተር ኦባማ ለሀገሪቱን ከፍተኛ ሲቪሎች ለመጨረሻ ጊዜ የሰጡት ሽልማት ነው።

“የነፃነት ሜዳሊያው አሜሪካ ውስጥ ማንኛውም ሰው ሀገሪቱን የተሻለች እንድትሆን ለመርዳት ይችላል የሚለውን ዕምነታችንን የምናከብርበት ነው” ብለዋል - ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ።

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

​ዛሬ መንፈሳችንን ከፍ ከፍ ያደርጉልንን አንድነታችንን ያጠናከሩልንና ወደ ዕድገት የገፉንን ልዩ የሆኑ አሜሪካውያን እናከብራለን ሲሉ ከተሸላሚዎቹ መካከልም በሲኒማ በሙዚቃ፣ በኪነ ጥብብ፣ በስፖርት፣ በሣይንስ እና የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ የተሰማሩ ይገኙበታል።

የማይክሮሶፍት ኩባኒያው መስራች ባለቤት ቢል ጌትስና ባለቤታቸው ሜሊንዳ ጌትስ በጎ አድራጎት ድርጅታቸው የጤና ጥበቃ ለድህነት እና ለረሃብ ማስወገጃ እንቅስቃሴዎች ሰላሣ ስድሥት ቢሊዮን ዶላር ለግሰዋል።

ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ

“ተባብረን ከሰራን ይቺን ዓለም የሚገባት ቦታ እንድትደርስ ለማድረግ እንችላለን በሚለው የተስፋ ስንቃቸው እኛንም እያነቃቁን ናቸው” ብለዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ፕሬዚዳንት ኦባማ ለሲቪሎች ታላቅ የክብር ኒሻን ሸለሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:47 0:00

XS
SM
MD
LG