በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ኦባማ የሥልጣን ዘመናቸው ከማብቃቱ በፊት የውጭ ሃገራት ጉብኝት ሊያደርጉ ነው


ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የፕሬዚዳንትነት ሥልጣናቸው ከማብቃቱ በፊት የመጨረሻ የውጭ ሃገራት ጉብኘት ለማካሄድ ዛሬ ይጓዛሉ።

ከውጭ ሀገራት መሪዎች ጋር በሚያካሄዱት ውይይት አብይ ርዕስ የሚሆነው የተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጉዳይ እንደሚሆን አማካሪዎቻቸው ይጠብቃሉ።

ምክትል የብሔራዊ ፀጥታ አማካሪ ቤን ሮዳስ በገለፁት መሠረት ፕሬዚዳንት ኦባማ ጀርመን፣ ግሪክና ፔሩ ይሄዳሉ።

ይህም ለዩናይትድ ስቴትስ ቅርብ ወዳጅ ሀገሮች የአንድነት ስሜት ለመግለፅና

“ለጠንካራና ለተዋሀደች አውሮፓ ድገፍ ለመስጠት ነው”

በመጪው ረዕቡ ግሪክ ላይ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲስ ሲፕረስ ጋር እንደሚነጋገሩ ሮዳስ ገልፀዋል።

የግሪክ ህዝብ የገጠመውን የኤኮኖሚ ቀውስ ለመወጣት ላደረገው ጥረት ድጋፋቸውን እንደሚገልፁ ምክትል የብሔራዊ አማካሪው ጠቁመዋል።

የጀርመን ቻንስለር አንጌላ መርከል
የጀርመን ቻንስለር አንጌላ መርከል

​የጀርመን ቻንስለር አንጌላ መርከል በመጪው ሀሙስ ፕሬዚዳንት ኦባማን ያስተናግዳሉ።

መርከል በመላ የፕሬዚዳንትነታቸው ጊዜ ቅርብ አጋራቸው እንደነበሩ ሮዳስ አስገንዝበዋል።

የብሪታንያ፣ የፈረንሣይ፣ የኢጣልያና የስፔን መሪዎችም ሀሙስ ለሚደረገው ስብሰባ ወደ በርሊን ይጓዛሉ።

XS
SM
MD
LG