ዋሺንግተን ዲሲ —
ይሁን እንጂ ይህ ከቤተሰቡ ጋር ከሁለት ዓመታት በፊት ወደ አሜሪካ የመጣው ወጣት ያደረሰው ጥቃት ኮለምበስ ከተማ ከሚገኘው የሙስሊም ማኅበረሰብ በላይ የተነካ የኅብረተሰብ ክፍል የለም፤ ልጁ ራሱ በግሉ በፈፀመው ተግባር ሃይማኖታችን ሃላፊነት የለበትም በማለት እያስገነዘቡ ናቸው።
አራሽ አራብሳዲ ከኦሃዮዋ ኮለምበስ ከተማ ያጠናቀረውን ዘገባ ያድምጡ፡፡
በዩናይትድ ስቴትስ ኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሶማሊያዊ ስደተኛ በሚያሽከረክረው መኪና ሰዎችን በመግጨትና በስለት በመውጋት ጉዳት ማደርሱን ተከትሎ የአካባቢው ማኅበረሰብ ተማሪው ይህን ጥቃት ለማድረስ ምን እንደገፋፋው ለመረዳት አዳግቶት ቆይቷል፡፡