ዋሺንግተን ዲሲ —
ጊሊአኒ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግነት ሥራ ልምድ ቢኖራቸውም በውጭ ጉዳዮች ፖሊሲ ጉዳይ ግን ከቀደሙት ባለሥልጣናት ጋር አይመጣጠኑም።
ጊሊአኒ በዶናልድ ትራምፕ የምረጡኝ ዘመቻ ወቅት፤ ጠንካራ ደጋፊ እንደነበሩ ይታወቃል።
በሌላም በኩል በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ሊካተቱ ይችላሉ የሚባሉት፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀደሞው የዩናይትድ ስቴትስ አምባሣደር ጆን ቦልተን ናቸው።