የአሜሪካ ድምፅ የተለያዩ ዝግጅት ክፍሎች ሪፖርተሮቹንና ቴክኒሻኖቹን አሠማርቶ ከተጓዙባቸው አካባቢዎችና ካደረጓቸው ስብሰባዎች ካስተላለፋቸው ዘገባዎቹ በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር በዘረጋው የሣተላይት ግንኙነት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የዋሺንግተን ዲሲ ንግግር በዓለም ዙሪያ ላሉ ተመልካቾች በጥራት እንዲደርስ አድርጓል።
በቁጥጥር ሥር የዋሉት ዘጠኝ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች የተያዙት ከስድስት ወር እስከ ሦስት ዓመት በእሥራት ሊያስቀጣ በሚችል ጥፋት ነው ሲሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ዘይኑ ጀማል ገልፀዋል።
“በዚህ ሥፍራ የሠረፀብኝ የክብር ስሜት፣ እጅግ የጨለሙ ቀኖቼ በዋጡኝ ጊዜ እየመጣ ሹክ ይለኝ፣ ይናገረኝ ነበር። እናም አሁን ውርደትን እፀየፍ ዘንድ ወደተማርኩበት ወደዚህ ሥፍራ እንደገና፣ ደግሞም እንደገና እመላለሳለሁ።” - ጃን መክኬን ወታደራዊ ሥልጠና ስለወሰዱበት የባሕር ኃይል አካደሚ ሲናገሩ
“እነሆ ንግሥት በዚያ ተኝታለች። በወርቅ በተለበጠ በረዥሙ አንፀባራቂ ካባዋ ተጠቅልላ፣ ከወርቅ ፍልጥላጮች የተሠፉ ያማሩ ጫማዎቿን ተጫምታ እነሆ ንግሥት እዚያ ብርሃን አንጣሪ ሆኖ በተሠራና በተዘጋ በሣጥኑ ውስጥ ተንጋላለች” የሶል ንግሥት አሬታ ፍራንክሊን .....
የኢትዮጵያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አድማ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋሽንግተን ዳላስ አየር ማረፊያ ሲደርሱም በአሜሪካ የሚኖሩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በ1981 ዓ.ም. በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ላይ መፈንቅለ-መንግሥት ተሞክሮ በነበረ ጊዜም የኩዴታው ጠንሳሾች ከሕዝባዊ ግንባር ሐርነት ኤርትራ መሪዎች ጋር ለመሥራት ጥረው እንደነበርና የደርግ ሥርዓት ሲወድቅም ኢሣያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያና ኤርትራን አንድ አድርገው እንዲመሩ ሃሣብ ቀርቦላቸው እንደነበረ ሻለቃ ዳዊት ገልፀዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ቅዳሜ፣ ሐምሌ 21/2010 ዓ.ም. ማውንት ቨርነን ፕሌስ በሚገኘው ኮንቬንሽን ሴንተር (801 Mt. Vernon Pl. NW, Washington, DC 20001) ግዙፍ ስብሰባ እንደሚደረግና በዚሁ ከቀኑ ሰባት ሰዓት እስከ አሥር ሰዓት ወይም ከ1PM እስከ 4PM በሚካሄደው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ለመገኘት የሚፈልጉ ሁሉ እንዲገኙ በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲና ሁሉን አቀፉ ጥምር ኮሚቴ ጥሪ አድርገዋል።
በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ላለፉት 18 ዓመታት ሠፍኖ የዘለቀው የጦርነት፣ የፀብና የኩርፊያ ዘመን አከተመ። በምትኩም የሰላም፣ የፍቅርና የነፃነት ዘመን ጠባ። በሚሊዮኖች ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ዘንድ እጅግ ስትናፈቅ የኖረችው ቀን እነሆ ደርሳ ታየች።
በዩናይትድ ስቴትሷ ቴኔሲ ግዛት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ አሜሪካዊያን ኢትዮጵያ ውስጥ እየታዩ ያሉ ለውጦችን እንደሚደግፉ ያሳወቁበትን ስብሰባ ባለፈው ዕሁድ ማካሄዳቸውን ከአስተባባሪዎቹ አንዱ ገልፀዋል።
የደቡብ ሱዳኑን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርን የሥልጣን ዘመን በሦስት ተጨማሪ ዓመታት ለማራዘም የሃገሪቱ ፓርላማ ያሳለፈውን ውሣኔ በብርቱ እንደሚያወግዝ በሪክ ማቻር የሚመራው “የሱዳን ሕዝብ ነፃ አውጭ ንቅናቄ - በተቃውሞ” የሚባለው ቡድን አሳውቋል።
ሞሪታንያ ዋና ከተማ ኑአክሸት ውስጥ ለተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት 31ኛ የመሪዎች ጉባዔ ድጋፏን እንደምትሰጥ ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች። ይህንን የሃገራቸውን መልዕክት ያስተላለፉት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ሄዘር ኑወርት ትናንት ባወጡት መግለጫ ነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ እየታዩ ያሉ ለውጦች “ጥሩ ናቸው” የሚለው የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር /ኦብነግ/ ሰሞኑን የተጀመረው ድፍድፍ የከርሰ-ምድር ዘይትና የተፈጥሮ ጋዝ የሙከራ ምርት በአስቸኳይ እንዲቆም እንደሚፈልግ አስታውቋል።
ዶ/ር አብይ አሕመድ አሜሪካን በመጭው ወር ሲጎበኙ በሚያደርጉላቸው አቀባበል ላይ የተነጋገሩ ዋሺንግተን ዲሲና በአካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያን-አሜሪካዊያን “ዛሬ እየተጠራጠሩ ያሉ ሁሉ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን እንዲቆሙና እንዲደግፏቸው” ጥሪ አስተላልፈዋል።
የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የጋራ ልማት ባለሥልጣን /ኢጋድ/ የተቋሙ ከፍተኛ አማካሪ የነበሩትን ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር ዓለምሰገድን አሰናብቷል።
ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ላለፉት 18 ዓመታት የዘለቀችበት “ጦርነትም ሰላምም የሌለበት ሁኔታ እንዲያበቃ” በሚል የአልጀርሱን ስምምነትና የሄጉን የድንበር ኮሚሽን ውሣኔ እንደምትቀበል መንግሥቷ አስታውቋል። ከኤርትራ በኩል ግን የተሰጠ ምላሽ የለም።
ጀረማይ ራንዴል ባለፈው ዓመት ከምሥራቅ አፍሪካ ወደ አሜሪካ የገባችውን ሚስቱን ከማግባቱ ጥቂት ቀደም ብሎ ሐይማኖቱን ወደ እሥልምና ቀይሯል። ሐይማኖት መቀየር ብዙ አዳዲስ ፈተናዎችን አብሮ ይዞ የሚመጣ የመሆኑ ነገር እርግጥ ሆኖ ሳለ ሙሽሮቹ ከጫጉላ ሽርሽራቸው እንደተመለሱ ለጀረማይ የመጀመሪያው የሆነውን ራማዳን ፃም አብረው ጀምረዋል።
ሰሜን ኮሪያ ወደ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ የምትቀላቀል ከሆነና ከዓለምአቀፍ አጋሮች ጋር እንድትገድ የሚፈቀድላት ከሆነ ከአፍሪካ ጋርም አጠቃላይ የንግድ ዕድገት ሊኖራት እንደሚችል ዋና መሥሪያ ቤቱ ፕሪቶሪያ የሆነው የደኅንነት ጥናት ተመራማሪ ዛካሪ ዶነንፌልድ አመልክተዋል።
የግብፅ መንግሥት በመብቶች ተሟጋቾች፣ በኢንተርኔት ላይ ፀሐፍት ወይም ብሎገሮችና በጋዜጠኞች ላይ እየወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ቢሮ በብርቱ አውግዟል።
ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ውስጥ የተቀሰቀሰው ኢቦላ በሰሜን ምዕራብ ገጠር እና በምባንዳካ ከተማ እየተስፋፋ መምጣቱ አሁን ሌሎች ሃገሮችንም እያሰጋ ነው።
ተጨማሪ ይጫኑ