በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለኢቦላ ምላሽ የኢትዮጵያ ዝግጅት


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ውስጥ የተቀሰቀሰው ኢቦላ በሰሜን ምዕራብ ገጠር እና በምባንዳካ ከተማ እየተስፋፋ መምጣቱ አሁን ሌሎች ሃገሮችንም እያሰጋ ነው።

ኢቦላ መከሰቱን የኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የዓለም የጤና ድርጅት ካረጋገጡ ከሚያዝያ ሃያ አምስት ወዲህ እየወጡ ባሉ ሪፖርቶች ከሃምሳ ሰው በላይ በበሽታው የተያዘ ሲሆን ከመካከላቸው ግማሽ ያህሉ ሞተዋል።

ወረርሽኙ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ለመከላከል መንግሥት በምክትል ጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ የሚመራ የኢቦላ ምላሽ ብሄራዊ ግብረኃይል አቋቁሞ በመላ ሃገሪቱ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎችና የቁጥጥርና ምላሽ አማካሪ አቶ አስቻለው አባይነህ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

በሁሉም የሃገሪቱ ዓለምአቀፍ ጣቢያዎች ላይ፣ በወሰን አካባቢዎችና መተላለፊያ ኬላዎች፣ በስደተኞች መጠለያዎች ውስጥ ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገ መሆኑን አቶ አስቻለው አመልክተዋል።

በቃለ-ምልልሱ ውስጥ የተቀሱ ቁጥሮች ባለፈው ሣምንት የነበሩ ናቸው።

ለሙሉው ቃለ-ምልልስ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ለኢቦላ ምላሽ የኢትዮጵያ ዝግጅት
please wait

No media source currently available

0:00 0:30:08 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG