በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዶ/ር አብይ የአሥመራ ጉብኝት በምሁራን ግምገማ

 ዶ/ር ተስፋማርያም መሃሪ (ግራ) እና ፕ/ር ብሩክ ኃይሉ (ቀኝ) ዶ/ር ተስፋማርያም መሃሪ (ግራ) እና ፕ/ር ብሩክ ኃይሉ (ቀኝ)
ዶ/ር ተስፋማርያም መሃሪ (ግራ) እና ፕ/ር ብሩክ ኃይሉ (ቀኝ) ዶ/ር ተስፋማርያም መሃሪ (ግራ) እና ፕ/ር ብሩክ ኃይሉ (ቀኝ)

በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ላለፉት 18 ዓመታት ሠፍኖ የዘለቀው የጦርነት፣ የፀብና የኩርፊያ ዘመን አከተመ። በምትኩም የሰላም፣ የፍቅርና የነፃነት ዘመን ጠባ። በሚሊዮኖች ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ዘንድ እጅግ ስትናፈቅ የኖረችው ቀን እነሆ ደርሳ ታየች።

በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ላለፉት 18 ዓመታት ሠፍኖ የዘለቀው የጦርነት፣ የፀብና የኩርፊያ ዘመን አከተመ። በምትኩም የሰላም፣ የፍቅርና የነፃነት ዘመን ጠባ። በሚሊዮኖች ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ዘንድ እጅግ ስትናፈቅ የኖረችው ቀን እነሆ ደርሳ ታየች።

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጉብኝት በሁለቱ ሃገሮች ግንኙነት አዲስ ምዕራፍ መፍጠሩን የሚናገሩ አስተያየቶች ገዥውን ቦታ ይዘዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የአሥመራ ጉዞ እና ትርጉም በኦሃዮ ዩኒቨርሲቲና በኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ብሩክ ኃይሉና (የኢትዮጵያ ተወላጅ) እንዲሁም በለንደኑ ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር ዶ/ር ተስፋማርያም መሃሪ (የኤርትራ ተወላጅ) ጉብኝቱ እየተካሄደ ሳለ ግምገማቸውን ለቪኦኤ ሰጥተው ነበር።

ፕ/ር ብሩክ የሁለቱ ሃገሮች ጦርነት እንዳበቃ በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ምክትል አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በዚያ የጦርነት ወላፈን ወቅት የሃገሪቱ የዓለምአቀፍ ማኅበረሰብ ቃል አቀባይ ያህል ነበሩ። ዶ/ር ተስፋማርያም በኢትዮጵያና በኤርትራ፣ እንዲሁም በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢያዊ ግንኙነቶች ላይ ጥናቶችን አካሄደዋል።

ሁለቱም ምሁራን የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር ተነሳሽነትና የሰላም ጥረት፤ የኤርትራውን ፕሬዚዳንትም በጎ ምላሽ ሰጥቶ አሥመራ ላይ የሞቀ አቀባበል ማድረግ በአድናቆት ሊታይ የሚገባው እንደሆነ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ግን “ኤርትራ በበረቱ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎች በተቃዎሚዎችና በሌሎችም የምትከሰስ ሃገር ሆና ሳለች እንዴት ነው ኢትዮጵያ እንዲህ ያለ ፍቅርና ግንኙነት ልትመሠርት የምትችለው?” የሚል ብዙዎች ለሚያነሱት ጥያቄም መልስ ሰጥተዋል።

ሙሉውን ውይይታቸውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የዶ/ር አብይ የአሥመራ ጉብኝት በምሁራን ግምገማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:22:28 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG