በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቴኔሲ ትውልደ-ኢትዮጵያ ድጋፍና ጥያቄ


በዩናይትድ ስቴትሷ ቴኔሲ ግዛት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ አሜሪካዊያን ኢትዮጵያ ውስጥ እየታዩ ያሉ ለውጦችን እንደሚደግፉ ያሳወቁበትን ስብሰባ ባለፈው ዕሁድ ማካሄዳቸውን ከአስተባባሪዎቹ አንዱ ገልፀዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ ጥቁሮች የመብቶችና የነፃነት ተጋድሎ ውስጥ ግዙፍ ታሪክ ባላት ቴኒሲ ግዛት ውስጥ የሚኖሩት ትውልደ-ኢትዮጵያ ሁሉ ሰሞኑን አዲስ ዓይነት የመነቃቃት ስሜት እንዳላቸው ነው የአስተባባሪያቸው ግብረኃይል አባል አቶ ፀሐይ ደመቀ ለቪኦኤ የተናገሩት።

ናሽቪል ላይ ባለፈው ዕሁድ፤ ሰኔ 24/2010 ዓ.ም. የተሰበሰበው በከተማዪቱና አካባቢዋ የሚኖር፣ ሜምፊስ ከምትባለው ሌላ ግዙፍ ከተማ ሳይቀር የተጠራራ ኢትዮጵያዊና ትውልደ-ኢትዮጵያ መሆኑን ገልፀዋል።

ስብሰባው በስፋቱ ቀድሞ አይተውት የማያውቁት እንደነበርም አመልክተዋል አቶ ፀሐይ።

በስብሰባቸው ማብቂያም ባለአራት ነጥብ የአቋም መግለጫም አውጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በመጭው ሐምሌ አሜሪካን ሲጎበኙ ጎራ ብለው እንዲያነጋግሯቸውም ጠይቀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የቴኔሲ ትውልደ-ኢትዮጵያ ድጋፍና ጥያቄ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:43 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG