በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦብነግ “ዘይቱን ማውጣት በአስቸኳይ ይቁም” ይላል

 ኦብነግ “የኦጋዴን ብሔራዊ ባንዲራ” የሚለው ባንዲራ /ፎቶ - ከዊኪፔድያ የተገኘ/
ኦብነግ “የኦጋዴን ብሔራዊ ባንዲራ” የሚለው ባንዲራ /ፎቶ - ከዊኪፔድያ የተገኘ/

ኢትዮጵያ ውስጥ እየታዩ ያሉ ለውጦች “ጥሩ ናቸው” የሚለው የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር /ኦብነግ/ ሰሞኑን የተጀመረው ድፍድፍ የከርሰ-ምድር ዘይትና የተፈጥሮ ጋዝ የሙከራ ምርት በአስቸኳይ እንዲቆም እንደሚፈልግ አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ እየታዩ ያሉ ለውጦች “ጥሩ ናቸው” የሚለው የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር /ኦብነግ/ ሰሞኑን የተጀመረው ድፍድፍ የከርሰ-ምድር ዘይትና የተፈጥሮ ጋዝ የሙከራ ምርት በአስቸኳይ እንዲቆም እንደሚፈልግ አስታውቋል።

ሰሞኑን ለቪኦኤ ቃላቸውን የሰጡት የግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ ሃሰን አብዱላሂ ዘይት እየወጣ ያለበት አካባቢ እንዲሁም የጦርነት ቀጣና በመሆኑ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ሳይገኝ የተጀመረው ሥራ ሰላሙን ይበልጥ አደጋ ላይ ሊጥለው ይችላል ብለዋል።

ኢትዮጵያዊነትና የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት አስመልክቶ የተጠየቁት አቶ ሃሰን ዕድሉን ሕዝቡ እራሱ እንዲወስን መደረግ አለበት ብለዋል።

ግንባሩ የሥራ አስፈፃሚውን የሦስት ቀናት ጉባዔ ባለፈው ዓርብ አጠናቅቆ የማዕከላዊ ኮሚቴውን ጉባዔ ለሰባት ወይም ለስምንት ቀናት እያካሄደ መሆኑንም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

የሚገኙበትን ሥፍራ “የአፍሪካ ቀንድ” ከማለት ውጭ በትክክል የት እንደሆነ አቶ ሃሰን ለመግለፅ አልፈለጉም።

ለሙሉው ቃለ-ምልልስ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኦብነግ “ዘይቱን ማውጣት በአስቸኳይ ይቁም” ይላል
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:01 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG