በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢጋድ ኢትዮጵያዊውን አማካሪ ከሥራ አሰናበተ


ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር ዓለምሰገድ /የኢጋድ ማስታወቂያ በጋዜጣ/
ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር ዓለምሰገድ /የኢጋድ ማስታወቂያ በጋዜጣ/

የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የጋራ ልማት ባለሥልጣን /ኢጋድ/ የተቋሙ ከፍተኛ አማካሪ የነበሩትን ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር ዓለምሰገድን አሰናብቷል።

ስለኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር ዓለምሰገድ የተፃፈ የኢጋድ ደብዳቤ
ስለኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር ዓለምሰገድ የተፃፈ የኢጋድ ደብዳቤ

የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የጋራ ልማት ባለሥልጣን /ኢጋድ/ የተቋሙ ከፍተኛ አማካሪ የነበሩትን ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር ዓለምሰገድን አሰናብቷል።

በኢጋድ ዋና ፀሐፊ በአምባሳደር ማሕቡብ ሙአሊም የተፈረመ ደብዳቤ ባለሥልጣኑ የኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር ዓለምሰገድን አገልግሎት ማቋረጡን ይናገራል።

ይህ ሰኞ፣ ሰኔ 18/2010 ዓ.ም. የተፃፈ ደብዳቤ ስለኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር ዓለምሰገድ መሰናበት ዝርዝር አላሰፈረም። ይሁን እንጂ ሥራቸውን ያስቆማቸው በዚያኑ ቀን መሆኑን አስታውቆ የአደጋን ንብረት ሁሉ ከትናንት በስተያ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ተኩል በፊት እንዲያስረክቡ አዝዟል።

ስለኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር ዓለምሰገድ ድንገተኛና የተጣደፈ መሰናበት ተጨማሪ ማብራሪያ ለመጠየቅ የኢጋድን ባለሥልጣናት ለማግኘት እየጣርን እንገኛለን። ቃል አቀባዩን አብዱላሂ ቡሱሪን ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት ለጊዜው አልተሣካም። ይሁን እንጂ ኢጋድ ኮ/ል ገብረእግዚአብሄርን ማሰናበቱንና የኢጋድ ውክልና እንደሌላቸው የሚገልፅ ማስታወቂያ በኬንያ ጋዜጦች ላይ ወጥቷል። ኮ/ል ገብረእግዚአብሄርን እራሣቸውንም ለማግኘት ባደረግነው ሙከራ ስልካቸውን አንስተው መልሰው እንደሚደውሉ ተናግረው ተዘግቷል። በተገኙ ጊዜ እርሣቸው የሚሉትን ይዘን እንመለሣለን።

ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር ዓለምሰገድ /የኢጋድ ማስታወቂያ በጋዜጣ/
ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር ዓለምሰገድ /የኢጋድ ማስታወቂያ በጋዜጣ/

በሌላ በኩል ሶማሊያ ውስጥ በቅርቡ የተካሄደን ምርጫና ተዓማኒነቱን በበላይነት ይከታተል የነበረ በፓርላማው የተቋቋመ ቡድን በሊቀመንበርነት ይመሩ የነበሩ የሚኔሶታ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር አብዲ ኢስማኢል ሳማታር ስለ ኮ/ል ገብረእግዚአብሄር ሲናገሩ “በሶማሊያ ፖለቲካ ላይ ጫና ለማሳደር በኢጋድ ሽፋን እንዲሠሩ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተላኩ ናቸው” ብለዋቸዋል። በመሆኑም የሶማሊያ ፖለቲከኞች፣ እንደራሴዎችና ሌሎችም በየወቅቱ “እንደ ንብ” ሲከብቧቸው ማየታቸውን ተናግረዋል።

የኢጋድን ውሣኔ አስመልክቶ ግን የተጣደፈው ውሣኔ የሚጠቁማቸው ውሣኔው የኢጋድ ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የፀጥታ ተቋም ለውጥ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ፕሮፌሰር ሳማታር ገልፀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG