የኢትዮጵያ አቪየሽን "አባት" ተብለው የሚታወቁት ኮሎኔል ጆን ቻርለስ ሮቢንሰን በክብር ታስበዋል።
ደቡብ ሱዳንን አሁን ወዳለችበት ቀውስና መከራ እንድታሽቆለቁል ምክንያት ሆነዋል ያሏቸው ተፋላሚ ኃይሎች መሪዎች የአሁን ምግባራቸውን እንዲለውጡ ለማስገደድ የሚቆነጥጡ የገንዘብና ሌሎችም እርምጃዎች እንዲወሰዱባቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአጣዳፊ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርክ ላውኮክ ጥሪ አስተላለፉ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ የዓለም ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ምሥረታ ሰባኛ ዓመትን ለማክበር ወደ ማሊ ሄደዋል። ምዕራብ አፍሪካዊቱ ማሊ ሚኑስማ በሚል ምኅፃር የሚጠራው የመንግሥታቱ ድርጅት ኃይል የሚገኝባት ሃገር ስትሆን ተልዕኮውን ለማጠናከር እንደሚሠሩ ዋና ፀሐፊው ቃል ገብተዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ እሥር ላይ የቆዩት የግንቦት ሰባት መሪ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ይፈታሉ ተብሎ ሲጠበቅ ውሏል።
በተለያዩ የምሥራቅ አፍሪካ አካባቢዎች ሰሞኑን እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ብዙ ሕይወት ማጥፋቱና በመቶዎች ሺሆች የሚቆጠር ሰው ማፈናቀሉ እየተነገረ ነው። በከበደው ዶፍ በብዛት እየተጎዱ ያሉት ኬንያ፣ ሶማሊያና ርዋንዳ መሆናቸው ታውቋል።
በቅዱስ ራማዳን ወር የሚከናወነው የፆም ሥርዓት አላህን ለመፍራት እንደሚያግዝ አዲስ አበባ የሚገኙ የእሥልምና መምህር በቪኦኤ ባስተላለፉት መልዕክት ተናግረዋል።
ሰሞኑን በውጥረት ውስጥ በሰነበቱት ሻኪሶና ለገደምቢ ከተሞች ዛሬ የመከላከያ ኃይል አባላት መግባታቸውን ነዋሪዎቻቸው ገልፀዋል። አዶላ ዋዩ ውስጥ ከትናንት በስተያ የተገደለ ጓደኛቸውን አስከሬን ለመቅበር ይሄዱ በነበሩ ባጃጅ ነጅዎች ላይ ድብደባ መፈፀሙም ተሰምቷል።
ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮች ዘላቂ መፍትኄ ለማስገኘት የሽግግር መንግሥት ማቋቋም ፍፁም አስፈላጊ ነው በሚሉ በአንድ በኩል በሌላ በኩል ደግሞ የሽግግር መንግሥት ቢቋቋም ጥሩ ቢሆንም ክፍትና ሁሉን አሣታፊ መድረክ እስከተፈጠረ ብቸኛ መንገድ ላይሆን ይችላል በሚሉ ሁለት አንጋፋ ምሁራን መካከል ውይይት አካሂደናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር በሕግ የተደነገገ ሥራ ቢኖረውም ሁሉም ጥቅል ነውና መንግሥቱ የሚፈፅማቸውን ተግባራት ዝርዝር እያበጀ ሃገር ያስተዳድራል፤ ሕዝብን ይመራል።
ምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ የፕሬስ ነፃነት ይዞታ እያሽቆለቆለ መምጣት በዘንድሮው የፕሬስ ነፃነት ቀን የመብቶች ተሟጋቾች ብዙ ትኩረት የሰጡት ጉዳይ ሆኗል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በያዙት ሕዝብን በቀጥታ የማግኘትና የማነጋገር ዘመቻ ገፍተዋል።
የወባን ሥርጭት ለማቆም ያስችላል ያሉትን አዲስ መላ መምታታቸውን አንድ እንግሊዛዊ ተመራማሪ አስታውቀዋል። ሰውን ሳይሆን ቢምቢዋን እራሷን ከወባ አምጭው ተውሣክ ወይም ቫይረስ መከላከል ወባን ምንጩ ላይ ማንጠፍ ነው ብለዋል ሳይንቲስቱ።
የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በዩናይትድ ስቴትስ የሦስት ቀናት ሙሉ መንግሥታዊ ጉብኝት ለማድረግ ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ገቡ።
የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በመጭው ሣምንት ከሰኞ እስከ ረቡዕ ዋሺንግተን ዲሲ ናቸው። ከአሜሪካ አቻቸው ጋር የሚያደርጓቸው ንግግሮች ፍሬ ያስገኙ ይሆን? የብዙዎች ጥያቄ ነው።
ኤችአር 128 ተብሎ የሚጠራውን የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ ያሳለፈው ውሣኔ እንዳይፀድቅ ለማስተጓጎል የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰባት መቶ ሚሊየን ብር በላይ በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ማውጣቱን አንድ የሕግ ባለሙያ ገለፁ።
ሶሪያ ላይ ትናንት የተካሄደው ጥቃት እጅግ የተዋጣ እንደነበርና ከዚህ በተሻለ ሁኔታ ሊከናወን እንደማይችል ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ አስታውቀዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ፣ እንግሊዝና ፈረንሣይ በሶሪያ ላይ የከፈቱት የተቀናጀ ጥቃት እየተካሄደ መሆኑን ፕሬዚዳንት ትረምፕ አስታወቁ።
ዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አምስት አባላት ሰሞኑን አራት የአፍሪካ ሃገሮችን በጎበኙበት ወቅት የተደረገላቸው አቀባበል የሞቀ እንደነበርና በትረምፕ አስተዳደር ላይ የተሰሟቸውን ቅሬታዎች የገለፁላቸው እንደነበሩ አመልክተዋል።
የዊኒ ማዲኪዜላ ማንዴላ አስከሬን የፊታችን ቅዳሜ በመንግሥታዊ የክብር ሥርዓት ወደ ዘለዓለማዊቸ ማረፊያው ይሸኛል። ዛሬ በሶዌቶው ኦርላንዶ ስታዲየም ሕይወታቸውን በክብር ሃሴት የዘከረ ሕዝባዊ ትርዒት ተከናውኗል።
ተጨማሪ ይጫኑ