በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሱ የሜሪላንድ ሙስሊም ቤተሰብ


ጀረማይ ራንዴል ባለፈው ዓመት ከምሥራቅ አፍሪካ ወደ አሜሪካ የገባችውን ሚስቱን ከማግባቱ ጥቂት ቀደም ብሎ ሐይማኖቱን ወደ እሥልምና ቀይሯል። ሐይማኖት መቀየር ብዙ አዳዲስ ፈተናዎችን አብሮ ይዞ የሚመጣ የመሆኑ ነገር እርግጥ ሆኖ ሳለ ሙሽሮቹ ከጫጉላ ሽርሽራቸው እንደተመለሱ ለጀረማይ የመጀመሪያው የሆነውን ራማዳን ፃም አብረው ጀምረዋል።

በሜሪላንድ ከተማ ቀመስ መኖሪያ አካባቢዎች ውስጥ ከሚገኙ መደበኛ ቤተሰቦች መካከል አንድ ወጣ ያለ ቤተሰብ ይኖራል።

ገና የጫጉላ ጊዜያቸውን ያልጨረሱት ሙሽሮች ይህ ዓመት አዲስ ተግዳሮት ይዞላቸው መጥቷል። ጀረማይ ሰልሞ ራማዳንን ሲፆም የዘንድሮው የመጀመሪያው ነው።

ጃራማይ ወደ ሙስሊምነት የተለወጠው የዛሬ ሦስት ወር ነው። ሂደቱ ረጅም እንደነበር ይናገራል። ያደገው በክርስትና ነው። አሁን ስለእሥልምና መማር ነበረበት። “እጅግ ጥሩ አስተማሪዬ ደግሞ ባለቤቴና ቤተሰቧ ናቸው” ይላል።

ትውልደ ኤርትራዋ አርያም መሐመድ ዛሬ የአሥር ዓመት ዕድሜው ላይ የሚገኘው፤ ጃራማያ ከቀድሞ ሚስቱ ያፈራው ኤርምያስ እናት ሆናለች። አባቱ ጃራማያና አርያም ከተጋቡ ጊዜ አንስቶም “እማማ” እያለ ነው ኤርምያስ የሚጠራት። አሁን አጠገባቸው ቆሟል። አርያም ደግሞ በሙስሊም ቤተሰብ ውስጥ ተወልዳ በእሥልምና ነው ያደገችው።

“እኔ የምፆመው ይህንን ልጅ ሳክል አንስቶ ነው። እንዲህ ዘው ብሎ በመግባቱ ጃራማይን አደንቀዋለሁ። እንዲያው የዋዛ አይደለም’ኮ፤ ቀላል አይደለም።” ብላለች።

በእውኑ ከባድ ነበር? ለጀረማይ....?

“ለእኔ ከባዱ ነገር ሐይማኖቴን መቀየሩ ነበር። ከዚያም የእኔና የእርሷ ግንኙነት ዜናውን ለወላጆቼ እንድናገር የሚያበቃኝ ደረጃ ላይ ‘ደርሷል ወይ?’ የሚለውም ሌላው ነበር። ስነግራቸው ግን በቀላሉ ተቀበሉት። አርያምን ስለወደዷት ይመስለኛል” ብሏል ጀረማይ።

ጀረማይ እሥልምናን የተቀበለው ባለፈው መጋቢት 8 በሜሪላንድ ሙስሊም ማኅበረሰብ ማዕከል ውስጥ ነበር። ዋሺንግተን ዲሲ የሚገኘው ፒው የምርምር ማዕከል ባወጣው ጥናታዊ ሪፖርት መሠረት እስልምናን ከሚቀበሉ አሜሪካዊያን መካከል ዘጠኝ ከመቶ የሚሆኑት ሐይማኖታቸውን የሚለውጡት በጋብቻ ምክንያት ነው።

“አንድን ሰው ሐይማኖቱን እንዲቀይር መጠየቅ ለእኔ እጅግ ከባድ ነገር ነበር። ቤተሰቡን የሚመለከት ሃሣብ ሲመጣ ደግሞ በጣም ነበር ያስፈራኝ። ነገር ግን እርሱ እንዳለው በጣም ደገፉን፤ ‘ለሁለታችሁም ትልቁ ቁም ነገር መተሳሰባችሁ ነው’ አሉን” አለች አርያም።

ጃራማይ የመጀመሪያ ባለቤቱን በካንሰር ምክንያት ያጣው የዛሬ አምስት ዓመት ነበር። ስለአርያም ሲናገር ግን በልዩ ፍቅር ነው።

“ከአርያም ጋር ስንገናኝ ለእኔ የተለየች ሰው መሆኗን ወዲያው ነው ያወቅኩት። እርሷን የመሰለች፤ እርሷን የምትጠጋ እንኳ ሴት በሕይወቴ ገጥማኝ አታውቅም” ይላል።

ለአንድ ወር ስለመፆም ብዙም አስቤ አላውቅም ነበር ይላል ጃራማይ። ራማዳን ገብቶ ከተጋመሰ በኋላ ግን እንደተለማማመደው፤ በጣም እንደቀለለው ነው የሚናገረው።

ኢድ ሙባረክ ሙስሊም ምዕመናን ...

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አዲሱ የሜሪላንድ ሙስሊም ቤተሰብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:56 0:00

አዲሱ የሜሪላንድ ሙስሊም ቤተሰብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:11 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG