በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ለመቀበል የኢትዮጵያዊያን ዝግጅት በአሜሪካ


ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ /ፎቶ - ፋይል/
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ /ፎቶ - ፋይል/

ዶ/ር አብይ አሕመድ አሜሪካን በመጭው ወር ሲጎበኙ በሚያደርጉላቸው አቀባበል ላይ የተነጋገሩ ዋሺንግተን ዲሲና በአካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያን-አሜሪካዊያን “ዛሬ እየተጠራጠሩ ያሉ ሁሉ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን እንዲቆሙና እንዲደግፏቸው” ጥሪ አስተላልፈዋል።

ዶ/ር አብይ አሕመድ አሜሪካን በመጭው ወር ሲጎበኙ በሚያደርጉላቸው አቀባበል ላይ የተነጋገሩ ዋሺንግተን ዲሲና በአካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያን-አሜሪካዊያን “ዛሬ እየተጠራጠሩ ያሉ ሁሉ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን እንዲቆሙና እንዲደግፏቸው” ጥሪ አስተላልፈዋል።

አሌግዛንድሪያ-ቨርጂንያ በሚገኘው ማርክ ሴንተር ዕሁድ፤ ሰኔ 17/2010 ዓ.ም. በተካሄደው ስብሰባ ላይ የተገኙት ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ ተሣታፊዎች ስብሰባቸውን የጀመሩት ባለፈው ቅዳሜ መስቀል አደባባይ ላይ በተደረገው ሰልፍ ላይ፣ እንዲሁም ባለፉት ዓመታት ለፍትሕ፣ ለመብቶች፣ ለነፃነት ድምፃቸውን ሲያሰሙ በየሥፍራው ለተገደሉ እንዲሁም ለተጎዱ ሁሉ ቆመው የሕሊና ፀሎት በማድረግና ክብር በመስጠት ነው።

“የትውልድ ድልድይ የዳያስፖራ ኮሚቴ” የሚባለው ስብስብ የፖለቲካ ድርጅቶች ውክልና የሌለውና በበጎ ፍቃደኛ ኢትዮጵያዊያን እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ መሆኑን አስተባባሪዎቹ ገልፀዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ አሜሪካ መምጣት ዜና ያስደሰታቸው መሆኑንና ድጋፋቸውን እንደሚሰጧቸው በስብሰባው ላይ የተገኙ የመድረክ ተናጋሪዎችና ሃሣቦቻቸውን ያንሸራሸሩት ተሣታፊዎች የገለፁ ሲሆን አስተዳደራቸው እንዲያተኩርባቸው እንደሚፈልጉ ከጠቋቆሟቸው ሃሣቦች መካከል “መንግሥታቸው በታማኝ ካድሬዎች ሳይሆን በዕውቀት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን፣ በውጭ ላሉ ኢትዮጵያዊያን የመንታ ዜግነት ጉዳይ እንዲታሰብ” የሚሉና ሌሎችም ይገኙባቸዋል።

በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በኩልም በሃገሪቱ የምጣኔ ኃብት ልማት ላይ በንቃት ለመሣተፍ፣ ወደሃገር የሚገባ የውጭ ምንዛሪ ማዕቀብን በማንሳትና ፍሰቱን በማስፋት፣ በተለያዩ የዕውቀትና የሙያ ዘርፎች ወደሃገር እየገቡ አገልግሎት በመስጠት እንዲተጉና በሃገሪቱ ግንባታ ላይ እንዲተጉም ጥሪዎች ተሰምተዋል።

አዘጋጆቹ ዋሺንግተን ዲሲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር አብረው እየሠሩ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን ከ“ትውልድ ድልድይ” ሌላም የተለያዩ ቡድኖች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚደረጉ አቀባበሎችና መስተንግዶዎች ላይ እያስተባበሩ መሆናቸውን እየገለፁ ናቸው።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ለመቀበል የኢትዮጵያዊያን ዝግጅት በአሜሪካ
please wait

No media source currently available

0:00 0:43:48 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG