በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትረምፕና የኡን መገናኘት ትርጉም ለአፍሪካ


ዛካሪ ዶነንፌልድ
ዛካሪ ዶነንፌልድ

ሰሜን ኮሪያ ወደ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ የምትቀላቀል ከሆነና ከዓለምአቀፍ አጋሮች ጋር እንድትገድ የሚፈቀድላት ከሆነ ከአፍሪካ ጋርም አጠቃላይ የንግድ ዕድገት ሊኖራት እንደሚችል ዋና መሥሪያ ቤቱ ፕሪቶሪያ የሆነው የደኅንነት ጥናት ተመራማሪ ዛካሪ ዶነንፌልድ አመልክተዋል።

ሰሜን ኮሪያ ወደ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ የምትቀላቀል ከሆነና ከዓለምአቀፍ አጋሮች ጋር እንድትገድ የሚፈቀድላት ከሆነ ከአፍሪካ ጋርም አጠቃላይ የንግድ ዕድገት ሊኖራት እንደሚችል ዋና መሥሪያ ቤቱ ፕሪቶሪያ የሆነው የደኅንነት ጥናት ተመራማሪ ዛካሪ ዶነንፌልድ አመልክተዋል።

በአፍሪካ ሃገሮችና በፒዮንግያንግ መካከል ያለው ግንኙነት በአብዛኛው በምሥራቁና በምዕራቡ ዓለም ለአሥሮች ዓመታት ዘልቆ በነበረው ቀዝቃዛ ጦርነት መንፈስ የተቃኘ እንደሆነ ያስታወሱት ዶነንፌልድ አፍሪካ በቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረትና በኮምዩኒስት አጋሮቿ በአንድ ወገን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በምዕራቡ ዓለም መካከል ይካሄድ የነበረው የእጅ አዙር የፍልሚያ አውድ እንደነበረች አመልክተው በዚያ ሁኔታ ውስጥ ኮሪያ የጦር መሣሪያ ለነፃነት ትግሎችና ሌሎችም ግጭቶች ማካሄጃ ትሸት እንደነበር ገልፀዋል።

ሰሜን ኮሪያ ከአፍሪካ ጋር በንግዱም መስክ ሆነ በሌላው ያላት ግንኙነት የሰፋ ባይሆንም እንደዚምባብዌና ናሚቢያ ካሉ የደቡባዊ አፍሪካ ሃገሮች ጋር ግን የቆዩና የጠበቁ ግንኙቶች እንዳሏት ዶናንፌልድ ጠቁመዋል።

ለሰሜን ኮሪያ ንግድ አፍሪካ ከአውሮፓ ኅብረት ቀጥሎ ያለች ሸሪኳ ስትሆን ዶነንፌልድ በጠቀሱት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ መሠረት ከአራት እስከ አምስት ከመቶ የሚሆን የንግድ ልውውጥ ድርሻ እንዳላቸው አመልክተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የትረምፕና የኡን መገናኘት ትርጉም ለአፍሪካ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:31 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG