የግብፅ መንግሥት የወሰደው እርምጃ ሃሣብን በመግለፅ ነፃነት፣ በመደራጀት ወይም በማኅበር በመሰባሰብና በመሰብሰብ መብቶች ላይ “እየተፈፀመ ያለ ጥሰት ወይም ረገጣ ነው” ሲል ቢሮው ከስሷል።
“የተጭበረበሩ ወይም ትክክለኛ ያልሆኑ ዜናዎችን ይፅፋሉ፣ ያወራሉ” በሚል “እውነትነት የሌለው” ሲል ቢሮው በጠራው ምክንያት ባለፉ ጥቂት ሣምንታት ታዋቂ አክቲቪስቶችን፣ ብሎገሮችንና ጋዜጠኞችን እየያዘ ማሰሩንና ምርመራዎችን እያካሄደባቸው መሆኑን አመልክቷል።
ሃሣባቸውን የመግለፅ መብታቸውን ስለተጠቀሙ ብቻ ስንት ሰዎች ተይዘው እንደታሠሩ እንደማይታወቅ የቢሮው ቃል አቀባይ ራቪና ሻምዳሳኒ ገልፀዋል።
ጉዳያቸው አግባብ ባለው ሕጋዊ መንገድ መታየት ያለበት የመሆኑ ግዴታ ባለመከበሩ ምክንያት አሁን ተይዘው የሚገኙበት ሁኔታም ቢሮውን ከሚያሳስቡት ጉዳዮች አንዱ መሆኑን ሻምዳሳኒ አመልክተዋል።
ከውንጀላዎቹ መካከል በተራዘመ ጊዜ እሥራት ሊያስቀጡ የሚችሉ ክሦች እንደሚገኙባቸው ሻምዳሳኒ ጠቁመዋል።
የግብፅ ባለሥልጣናት የያዟቸውን አክቲቪስቶች፣ ብሎገሮችና ጋዜጠኞች በሙሉ ያለአንዳች ተጨማሪ ማንገራገር ፈጥነው እንዲለቅቁ የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ጠይቆ መንግሥቱ የገባባቸውን የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎች ዓለምአቀፍ ግዴታዎቹን እንዲያከብር አሳስበዋል።
በሌላ በኩል ሮይተርስ የዜና አውታር የግብፅን መንግሥታዊ የዜና ወኪል “ሜና”ን ጠቅሶ እንደገዘገበው ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ ኤል-ሲሲ መንግሥትን በመቃወም በሚል ተይዘው ለነበሩ 712 እሥረኞች ምህረት አድርገዋል።
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ