በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያና በኤርትራ ሰላም ጉዳይ - ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ

ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ
ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ

በ1981 ዓ.ም. በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ላይ መፈንቅለ-መንግሥት ተሞክሮ በነበረ ጊዜም የኩዴታው ጠንሳሾች ከሕዝባዊ ግንባር ሐርነት ኤርትራ መሪዎች ጋር ለመሥራት ጥረው እንደነበርና የደርግ ሥርዓት ሲወድቅም ኢሣያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያና ኤርትራን አንድ አድርገው እንዲመሩ ሃሣብ ቀርቦላቸው እንደነበረ ሻለቃ ዳዊት ገልፀዋል።

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያ በመግባታቸውና በሁለቱ ሃገሮች መካከል ሰላም በመበሰሩ የተሰማቸው ደስታ እስከማልቀስ እንዳደረሳቸው በዘመነ ደርግ የኤርትራ አስተዳዳሪ የነበሩት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ለቪኦኤ ገለፁ።

ሻለቃ ዳዊት ካለፈ ታሪክ እያጣቀሱ ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ የሁለቱ ሃገሮች ግንኙነት አሁን ወደደረሰበት ሁኔታ መለወጡ በስትራተጂ፣ አካባቢያዊ ደኅንነት፣ በምጣኔኃብት መተጋገዝና የሁለቱን ሃገሮች ሕዝቦች አንድነት በማጠናከር ላይ ለመሥራት አማራጭ የሌለው መንገድ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በ1981 ዓ.ም. በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ላይ መፈንቅለ-መንግሥት ተሞክሮ በነበረ ጊዜም የኩዴታው ጠንሳሾች ከሕዝባዊ ግንባር ሐርነት ኤርትራ መሪዎች ጋር ለመሥራት ጥረው እንደነበርና የደርግ ሥርዓት ሲወድቅም ኢሣያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያና ኤርትራን አንድ አድርገው እንዲመሩ ሃሣብ ቀርቦላቸው እንደነበረ ሻለቃ ዳዊት ገልፀዋል።

የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝቦች “የተለያዩ ሁለት ሕዝቦች ናቸው የሚሉ የተሣሣቱ ናቸው፤ እኔ በየትኛውም ፅሁፌና ንግግሬ እንዲህ ብዬ አላውቅም” ብለዋል።

ለሙሉው ቃለ-ምልልስ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኢትዮጵያና በኤርትራ ሰላም ጉዳይ - ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:31:31 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG