በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዶ/ር አብይ የአሜሪካ ጉዞ የፕሬስ መግለጫ

የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዋሽንግተን ዲሲ
የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዋሽንግተን ዲሲ

ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ቅዳሜ፣ ሐምሌ 21/2010 ዓ.ም. ማውንት ቨርነን ፕሌስ በሚገኘው ኮንቬንሽን ሴንተር (801 Mt. Vernon Pl. NW, Washington, DC 20001) ግዙፍ ስብሰባ እንደሚደረግና በዚሁ ከቀኑ ሰባት ሰዓት እስከ አሥር ሰዓት ወይም ከ1PM እስከ 4PM በሚካሄደው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ለመገኘት የሚፈልጉ ሁሉ እንዲገኙ በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲና ሁሉን አቀፉ ጥምር ኮሚቴ ጥሪ አድርገዋል።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የሚያደርጉትን ጉዞ አስመልክቶ ዋሺንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲና ከኤምባሲው ጋር እየተንቀሳቀሰ ያለው ሁሉን አቀፍ የአቀባበል ዝግጅት አብይ ኮሚቴ ዝርዝር መርኃግብርና መግለጫ እያወጣ ነው።

ኤምባሲው ዛሬ ለቪኦኤ ባሳወቀው መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋሺንግተን ዲሲ የሚገቡት ሐሙስ፣ ሐምሌ 19/2010 ዓ.ም. መሆኑን አረጋግጧል።

“የጥላቻና የልዩነት ግድግዳን አፍርሰን የፍቅርና የአንድነት ድልድይ እንገነባለን” በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የአሜሪካ ጉዞ ዋሺንግተን ዲሲ፣ ሎስ አንጀስና ሜኔሶታ ከተሞች ተገኝተው ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ አሜሪካዊያንን እንደሚያነጋግሩ የኤምባሲው መግለጫ አመልክቷል።

ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ቅዳሜ፣ ሐምሌ 21/2010 ዓ.ም. ማውንት ቨርነን ፕሌስ በሚገኘው ኮንቬንሽን ሴንተር (801 Mt. Vernon Pl. NW, Washington, DC 20001) ግዙፍ ስብሰባ እንደሚደረግና በዚሁ ከቀኑ ሰባት ሰዓት እስከ አሥር ሰዓት ወይም ከ1PM እስከ 4PM በሚካሄደው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ለመገኘት የሚፈልጉ ሁሉ እንዲገኙ በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲና ሁሉን አቀፉ ጥምር ኮሚቴ ጥሪ አድርገዋል።

በዚያው ዕለትም 1500 የሚሆኑ የተለያዩ የማኅበረብ ተጠሪዎች የሚጋበዙበት ሌላ ስብሰባም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንደሚደረግ ታውቋል።

ኮንቬንሽን ሴንተር አርባ አምስት ሺህ ሰው የመያዝ አቅም ያለው መሆኑን፣ በስብሰባው ላይ ለመገኘት ምዝገባም ሆነ ክፍያ እንደማያስፈልግ ኤምባሲው አስታውቆ በተለያዩ የሕብረተሰብ አካላትና በኤምባሲው ትብብር በተቋቋሙ ሁሉን አቀፍ የአቀባበል ዝግጅት ኮሚቴዎች ውስጥ ገብቶ በበጎ ፍቃል ለመሣተፍ የሚፈልግ ማንም ሰው መሣተፍ የሚችል መሆኑንም አክሎ ገልጿል።

ሎስ አንጀለስ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንሲል ጄነራል ፅህፈት ቤት አስተባባሪነትም በኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ ተነሳሽነት ተጨማሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ በምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስም የአቀባበል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕሁድ ሐምሌ 22/2010 ዓ.ም. በዚያ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር እንደዋሺንግተን ዲሲው ባለ መድረክ እንደሚገናኙ የኤምባሲው መግለጫ ይናገራል።

ዋሺንግተን ዲሲ ላይ የተቋቋመው ከሰማንያ በላይ የተለያዩ የኢትዮጵያዊያን መድረኮች፣ የሃይማኖቶች፣ የፆታ፣ የዕድሜ፣ የብሄር ብሄረሰብና ሌሎችም ስብጥሮች ያሏቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች መሆናቸውንም ኤምባሲው ገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚገኙባቸው መድረኮች ላይ ከውይይት በተጨማሪ ኢትዮጵያዊያኑ የሚያዘጋጇቸው የተለያዩ የኪነጥበብ፣ የግጥሞችና ጊዜውን የሚገልፁ መልዕክቶችን የማስተላለፊያ መሰናዶዎች እንደሚኖሩ ታውቋል።

ሎስ አንጀስና ሚኔሶታ ላይ ስለሚደረጉት ዝግጅቶችና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዩናይትድ ስቴትስ ቆይታቸው ወቅት ስለሚያከናውኗቸው ሌሎችም ሥራዎች እየተከታተልን ተጨማሪ ዝርዝሮችን በየወቅቱ ማቅረባችንን እንቀጥላለን።

ስለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የአሜሪካ ጉዞ በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የወጣ ጋዜጣዊ መግለጫ
ስለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የአሜሪካ ጉዞ በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የወጣ ጋዜጣዊ መግለጫ

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG