ዋሺንግተን ዲሲ —
ኤስ.ፒ.ኤል.ኤም.-አይ.ኦ. በሚል ምኅፃር የሚጠራው የደቡብ ሱዳኑ ተቃዋሚ ፓርቲ የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርን የሥልጣን ዘመን መራዘም ዜና የሰማው ከማኅበራዊ መገናኛዎች እንደሆነ ነው የባሕል የወጣቶችና የስፖርት ኮሚቴው ሊቀመንበር ማናሴ ዚንዶ ለቪኦኤ የገለፁት።
“እርምጃው - ብለዋል የኮሚቴው ሊቀመንበር ማናሴ ዚንዶ - የደቡብ ሱዳን መንግሥት ስንነጋገርበት ለቆየነው ዓይነት የሰላም ሂደት ቁርጠኛነት የሌለው መሆኑን ያመላክታል።
“ሕገ-መንግሥታዊ የሕግ የበላይነትንም ይፃረራል” ብለዋል።
በሌላ በኩል ግን ሂደቱ የተሣካ እንዲሆን ጁባ ላይ ያልተቋረጠ መንግሥት መኖርና የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ሥልጣን ላይ መቆየት አስፈላጊ ናቸው ብለው የሚያምኑ እንዳሉ ተጠይቀው ዚንዶ ሲመልሱ “ሳልቫ ኪር የሃገሪቱን የቀውስ ሁኔታ ተጠቅመው የሥልጣን ዘመናቸው ካለቀ በኋላ እዚያው ለመቆየት በጓሮ በር ለመግባት እያደረጉ ያሉት ኢ-ሕገመንግሥታዊ አካሄድ ነው” ብለውታል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ