በጎንደር ከተማ ከትላንት ጀምሮ በተፈጠረው ውጥረት ሳቢያ ሕይወት እየጠፋና ንብረት እየወደመ መሆኑ ተነገረ።
የወልቃይትን ሕዝብ የማንነት ጥያቄ በኮሚቴ አባልነት ከሚመሩት መካከል አራቱ ከጎንደር ከተማ ታፍነው ወዴት እንደደረሱ እንደማይታወቅ፣ አንድ የኮሚቴ አባል ደግሞ በግቢያቸው ውስጥ ተከበው እንደሚገኙ የኮሚቴው ፀሐፊ ነኝ ያሉ ለአሜሪካ ድምጽ አስታወቁ። አንድ የፌደራል እና የክልል ባለሥልጣን ግን አራቱ የኮሚቴ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውና ሌላኛው አባል በግቢያቸው በፌደራል ፖሊስ ተከበው እንደሚገኙ ተናግረዋል።
የአረና ትግራይ ፓርቲ የሥራ አመራር አባል የነበረው አቶ አብርሀ ደስታ ዛሬ ከእስር መፈታቱ ታወቀ። አቶ አብርሀ ከእስር መፈታት የነበረበት ከወራት በፊት ቢሆንም ፍርድ ቤት ተዳፍረሃል በሚል ምክንያት ጥፋተኛ ተብሎ ቅጣት ተጥሎበት ቆይቷል።
የፈዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀድሞ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ አመራር አባል አቶ ሃብታሙ አያሌው ወደ ውጭ አገር ሄዶ እንዲታከም ተጨማሪ የሃኪሞች ቦርድ ማረጋገጫ እንዲያቀርብ ጠየቀ።
አቶ ሃብታሙ አያሌው ለሕክምና ለመውጣት ያቀረበውን አቤቱታ የፈዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ‘ዳኛ አልተሟላም’ በማለት ዛሬም ውሳኔ ሳይሰጥ ቀረ።
የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ሰመጉ በአዲስ አበባ ከተማና አካባቢው ዜጎችን ከቤት ንብረት የማፈናቀል ድርጊት እንዲቆም ጥሪ አቀረበ።
ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ ሰኔ 26/2008 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ በሙሉዓለም አዳራሸ ሊያደርገው የነበረውን ሕዝባዊ ስብሰባ ለሌላ ጊዘ ማስተላለፉን የፓርቲው አመራር አስታውቋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትና ቀስቃሾች ለሕገወጥ ስብሰባ ቀስቅሳችኋል ተብለው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ነገሠ ተፈረደኝ ለቪኦኤ አስታወቁ፡፡
በኢትዮጵያ ህገ-መንግሥት መሠረት የማንነት ጥያቄ በሚያነሡ ዜጎች ላይ የሚፈፀም ግድያ፣ህገወጥ እስራት፣አፍኖ መሠወር፣መፈናቀልና፣ንብረት መንጠቅ በአስቸኳይ ይቁም ሲል የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ጥሪ አቀረበ።
የዩናይትስ ስቴትስ የዓለም አቀፍ የልማት ኤጄንሲ (ዩኤስኤአይዲ) ብሔራዊ የኤድስ መረጃና የምክር አገልግሎት ማዕከልን ለኢትዮጵያ መንግሥት አስረከበ።
የፈደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛው የወንጀል ችሎት በኢንተርነት አምደኛው በፍቃዱ ሃይሉ እና በአቃቤ ህግ ባለው ክርክር ላይ ሊሰጠው የነበረው ውሳኔ እንዳልደረሰለት አስታወቀ። ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮም ሰጥቷል።
ዓቃቢ ህግ ተከሳሶች ያቀረቧቸው መቃወምያዎች ሁሉ ውድቅ እንዲደረጉ ጠይቀዋል።ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ቆርጧል።
የሰማያዊ ፓርቲ የኦዲትና የኢንስፔክሽን ኮሚተ ሊቀ-መንበር የፓርቲው ብሔራዊ ምክር-ቤት በፓርቲው ውስጥ በአመራር ደረጃ ተፈጥሮ የነበረውን ችግር የሚፈታ አካል መፍጠሩን አስታወቁ።
ማክሰኞለት የተባበሩት መንግስታት የመብት አጣሪ ቡድን የኤርትራ ባለስልጣናት በዜጎቻቸው ላይ እየፈጸሙ ነው ያላቸውን ሰፊ የመብት ጥሰቶች፤ አስረድቶ የኤርትራ መሪዎች በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ወይንም በሌሎች የፍትህ ችሎቶች ክስ እንዲመሰረትባቸው መጠየቁ ይታወሳል።
ሰማያዊ ፓርቲ በባህር ዳር ከተማ ሊያካሂደው የነበረውን ሕዝባዊ ውይይት ለሌላ ጊዜ አስተላልፎ እንዲያስተዋውቀው የከተማው አስተዳደር አሳሰበ።
ዓቃቤ ሕግ በሽብር ወንጀል ክስ የመሰረተባቸው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ የወጣቶች ሊግ የቀድሞ ሊቀመንበር አቶ ደስታ ዲንቃና ሌሎች ሦስት ተጠርጣሪዎች ዛሬ የክስ መቃወሚያቸውን አቀረቡ።
ተጨማሪ ይጫኑ