በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የወልቃይት ኮሚቴ አባል በጎንደር ስለተወሰደው ርምጃ ይናገራሉ


የጎንደር ካርታ
የጎንደር ካርታ

የወልቃይትን ሕዝብ የማንነት ጥያቄ በኮሚቴ አባልነት ከሚመሩት መካከል አራቱ ከጎንደር ከተማ ታፍነው ወዴት እንደደረሱ እንደማይታወቅ፣ አንድ የኮሚቴ አባል ደግሞ በግቢያቸው ውስጥ ተከበው እንደሚገኙ የኮሚቴው ፀሐፊ ነኝ ያሉ ለአሜሪካ ድምጽ አስታወቁ። አንድ የፌደራል እና የክልል ባለሥልጣን ግን አራቱ የኮሚቴ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውና ሌላኛው አባል በግቢያቸው በፌደራል ፖሊስ ተከበው እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የኮሚቴው አባላቱ ታፍነው መወሰዳቸውንና አሁን የደረሱበት እንደማይታወቅ የገለጹት የዚሁ የወልቃይት ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ጸሐፊ መኾናቸውን የሚናገሩት አቶ አደራጀው ናኘው ናቸው።

አቶ አደራጀው ለቪኦኤ እንዳብራሩት አፋኝ ያሉዋቸው ኃይሎች አራቱን የኮሚቴ አባላት ጎንደር ከተማ ውስጥ ከሌሊቱ ዐሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ እንዴት እንደያዙዋቸው ዘርዝረዋል።

“ማንነታቸው አይታወቅም የፌደራል ልብስና ጭምብል ለብሰዋል እነዚህ ሰዎች መጀመሪያ አቶ አታላይ ዛፌን ቤቱን ሰብረው በመግባት በቁጥጥር ስር አውለውታል።” የሚሉት አቶ አደራጀው እሱን ጨምሮ በአጠቃላይ አራት ሰዎች ታፍነው መወሰዳቸውን ተናግረዋል።

የዚሁ ኮሚቴ አባል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ በወታደር ተከበው እንደሚገኙ እና ወደ ቤታቸውም ሦስት ቦንብ እንደተወረወረባቸው ተናግረዋል።

መለስካቸው አመሃ ዝርዝር አለው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የወልቃይት ኮሚቴ አባል በጎንደር ስለተወሰደው ርምጃ ይናገራሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:29 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG