በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰመጉ መንግሥት የማንነት ጥያቄ በሚያነሱ ዜጎች ላይ የሚፈፀም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንዲቆም ጥሪ አቀረበ


ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ
ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ

በኢትዮጵያ ህገ-መንግሥት መሠረት የማንነት ጥያቄ በሚያነሡ ዜጎች ላይ የሚፈፀም ግድያ፣ህገወጥ እስራት፣አፍኖ መሠወር፣መፈናቀልና፣ንብረት መንጠቅ በአስቸኳይ ይቁም ሲል የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ጥሪ አቀረበ።

ሰመጉ በ141ኛ ልዩ መግለጫው የወልቃይት፣የቅማንት እና የቁጫ እና የኮንቶማ ማህበረሰቦች ያነሱትን የማህበረሰብ ጥያቄ ተከትሎ ከ56 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን አስታወቀ። በመቶ ሚሊዮኖች ብር የሚገመት ንብረት እንደወደመም ገለፀ። ሌሎች የተለያዩ ጉዳቶች በዜጎች ላይ መፈፀማቸውንም ይፋ አድርጓል።

ቀድሞ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በመባል የሚታወቀ አሁን የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በሚል ስያሜ የሚታወቀው ለሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት ዛሬ ባወጣው 141 ኛ ልዩ መግለጫው አራት ማህበረሰቦች ባነሱት የማንነት ጥያቄ በተከተለው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ላይ አተኩሯል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ሰመጉ መንግሥት የማንነት ጥያቄ በሚያነሱ ዜጎች ላይ የሚፈፀም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንዲቆም ጥሪ አቀረበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:17 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG