አዲስ አበባ —
ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ ሰኔ 26/2008 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ በሙሉዓለም አዳራሸ ሊያደርገው የነበረውን ሕዝባዊ ስብሰባ ለሌላ ጊዘ ማስተላለፉን የፓርቲው አመራር አስታውቋል፡፡
በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት የፓርቲው አባላትና ሌሎቹም ከአንድ ሰው በስተቀር አሁንም አልተለቀቁም፡፡
ኮሚቴው ስብሰባውን ለማስተላለፍ የወሰነው በክልሉ መስዳድር ዕውቅና ያገኘውን ይህንን ህዝባዊ ስብሰባ የፀጥታ ዘርፉ አላውቅም በማለቱና ቅስቀሳ ሲያካሂዱ የነበሩትን የፓርቲውን አባላት በቁጥጥር ሥር ካዋለ በኋላ የተፈጠረውን አጠቃላይ ሁኔታ በመገምገም እንደሆነ አቶ ነገሠ አስረድተዋል፡፡
በቂጥጥር ሥር የዋሉትን ሰዎች ፖሊስ ዛሬ - ቅዳሜ ቃላቸውን ተቀብሎ ከመካከላቸው አንድ ሰው መፍታቱ ታውቋል፡፡
በቁጥጥር ሥር ያሉት አሥር ሰዎች በባህር ዳር ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እሥር ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ዛሬ ከረፋዱ ጀምሮ ፖሊስ ሙሉዓለም አዳራሽን ከብቦ እንደነበር አቶ ነገሠ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡