በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አብርሀ ደስታ ተፈታ


አቶ አብርሀ ደስታ
አቶ አብርሀ ደስታ

የአረና ትግራይ ፓርቲ የሥራ አመራር አባል የነበረው አቶ አብርሀ ደስታ ዛሬ ከእስር መፈታቱ ታወቀ። አቶ አብርሀ ከእስር መፈታት የነበረበት ከወራት በፊት ቢሆንም ፍርድ ቤት ተዳፍረሃል በሚል ምክንያት ጥፋተኛ ተብሎ ቅጣት ተጥሎበት ቆይቷል።

የአረና ትግራይ የሉአላዊነትና የዴሞክራሲ ፓርቲ የሥራ አመራር አባል የነበረው አቶ አብርሀ ደስታ ለሁለት ዓመት ታሥሮ ከቆየ በኋላ ዛሬ አመሻሹ ላይ ተለቅቋል፡፡

“ይሄ ነው የሚባል መጉላላት ዛሬ ባይደርስብኝም ከግቢው ለመውጣት ከምጠብቀው በላይ ጊዜው ረዝሞብኛል” በማለት አቶ አብርሀ የእስር ፍቺ ሂደቱን ለመግለፅ ሞክሯል። የፌደራሉ አቃቤ ህግ በጥቅምት ወር 2007 ዓ.ም በነዘላለም የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ክስ ከመሰረተባቸው አስር ሰዎች መካከል አንዱ አቶ አብርሀ ደስታ ነበር።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አቶ አብርሀ ደስታ ከእስር ተፈታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:38 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG