በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰማያዊ ፓርቲ በባህርዳር ከተማ ሊያካሂድ ያሰበው ሕዝባዊ ውይይት እንዲቀይር የከተማዋ አስተዳደር አሳሰብ


ሰማያዊ ፓርቲ በባህር ዳር ከተማ ሊያካሂደው የነበረውን ሕዝባዊ ውይይት ለሌላ ጊዜ አስተላልፎ እንዲያስተዋውቀው የከተማው አስተዳደር አሳሰበ።

የፓርቲው ሊቀ መንበር ገዢው ፓርቲ ይህ እርምጃ በመውሰዱ ሃሳብን የመግለጽ በነፃነትና የመደራጀት መብትን እንደዘጋ የሚያመለክት ነው ይላሉ።

ሰማያዊ ፓርቲ ሰኔ 8,2008 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ሰኔ 19,2008 ዓ.ም ፓርቲው በባህር ዳር ከተማ ከሚገኙ አባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር በዚሁ ከተማ ውይይት ለማካሄድ መርሃ-ግብር እንደያዘ ለከተማው አስተዳደር በደብዳቤ ማስታወቁ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሃላዩ መኮነን የጻፉትም ደብዳቤ ያመለክታል።

ይሀው ደብዳቤ በሚከተለው አንቀጽ ደግሞ ሰኔ 19, 2008 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ ሌላ ተግባራት ያሉ በመሆኑ ቀይራችሁ እንድታሳውቁን እናሳስባለን ይላል።

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ- መንበር አቶ ይልቃል ጌትነትን ተጨማሪ ማብራርያ ካለ ተጠይቀው ሲመልሱ እስከ ዛሬ ከነበራቸው ልምድ እንዲህ ዓይነት ደብዳቤ እንዳላጋጠማቸው ተናግረው በአገሪቱ ሃሳብ የመግለጽ በነፃነትና ሌሎች መብቶች ምን ያህል እንደተጣበቡ ያስረዳሉ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

ሰማያዊ ፓርቲ በባህርዳር ከተማ ሊያካሂድ ያሰበው ሕዝባዊ ውይይት እንዲቀይር የከተማዋ አስተዳደር አሳሰብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:56 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG