በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፈደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኢንተርነት አምደኛው በፈቃዱ ሃይሉ ጉዳይ ሌላ ቀጠሮ ሰጠ


የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የፈደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛው የወንጀል ችሎት በኢንተርነት አምደኛው በፍቃዱ ሃይሉ እና በአቃቤ ህግ ባለው ክርክር ላይ ሊሰጠው የነበረው ውሳኔ እንዳልደረሰለት አስታወቀ። ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮም ሰጥቷል።

ችሎቱ በሌላ በኩል የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ ወጣቶች ሊግ ሊቀመንበር አቶ ደስታ ዲንቃን ጨምሮ አራት ተጠርጣሪዎች ለተመሰረተባቸው የሽብር ወንጀል ክስ ላቀረቡት መቃወምያ የአቃቤ ህግን መልስ ተቀብሏል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ ቆርጧል።

የኢንተርነት አምደኛ በፍቃዱ ሃይሉ( ቀኝ የመጨረሻ)
የኢንተርነት አምደኛ በፍቃዱ ሃይሉ( ቀኝ የመጨረሻ)

የፈደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ19ኛው ወንጀል ችሎት ዛሬ በኢንተርነት አምደኛው በበፍቃዱ ሃይሉና በፈደራል አቃቤ ህግ ባለው ክርክር ላይ ውሳኔውን እንደሚያሰማ ይጠበቅ ነበረ። ይሁንና ፍርድ ቤቱ በችሎቱ እንዳስታወቀው መዝገቡ ቀደም ብሎ እንዳልቀረበለትና በችሎት ላይ እንደቀረበለት ተናግሯል።ከዚህም ጋር አያይዞ መዝገቡ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዲላክ የመጣለት ትእዛዝ እንዳለ አስታውቋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የፈደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኢንተርነት አምደኛው በፈቃዱ ሃይሉ ጉዳይ ሌላ ቀጠሮ ሰጠ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:16 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG