አዲስ አበባ —
የቀድሞ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ አመራር አባል አቶ ሃብታሙ አያሌው ለሕክምና ከአገር ውጪ ለመሄድ ያቀረበውን አቤቱታ የፈዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ አልተሟላም በማለት ዛሬም እንዳልወሰነ ተገለፀ።
ፍርድ ቤቱ በአቃቤ ህግና በእነ አቶ ሃብታሙ አያሌው መካከል ባለው ክርክር ላይ ውሣኔ ለማሰማትም ለአምስተኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ጠበቃው አቶ አምሃ መኮንን ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል መንግሥት ዳኛ አሟልቶ መጠበቅ እንደሚገባው ገልፀው በዳኛ አለመሟላት ሰበብ የውሣኔው መጓተት አግባብ አለመሆኑን አመልክተዋል፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡