በኢህአዴግና አጋሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባሏቸው መካከል በሚካሄድ ድርድር የሚደረስባቸው ድምዳሜዎች ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን ማሻሻል ቢያስፈልግ እንኳን ያን ለማድረግ ቁርጠኝነት እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለፓርላማው አስታወቁ።
የዲቪ ሎተሪ ማመልከቻ ቀን ከአሥር ቀናት በኋላ እንደሚጠናቀቅ አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አስታወቀ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሕግን ለማስከበር ታልሞ የወጣ ጊዚያዊ መፍትሔ እንጂ ዘላቂው መፍትሔ ግን ፖለቲካዊ እርምጃ እንደሆነ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር አስታወቁ፡፡
የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዮናታን ተስፋዬ ዛሬ ፍርድ ቤት አልቀረበም።
የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ለዛሬ፤ ዕሁድ ጥቅምት 13/2009 ዓ.ም ያዘጋጀውና እያካሄደ የነበረው የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብር ሳይጠናቀቅ በፀጥታ ኃይሎች ተቋርጧል፡፡
የነ አቶ ኃብታሙ አያሌውና የነ ሶሊያና ሽመልስ ጉዳይ በመጓተቱ ጠበቃቸው ስሞታ አሰሙ፡፡
የፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነት አፍሪካ በቴክኖሎጂ አጠቃቀሟ እመርታ ልታገኝበት የምትችልበትን እድል እንደሰጣት ተነገረ።
የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የኢትዮጵያው ፕሬዚዳንት ለፓርላማው ባሰሙት ንግግር አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል።
ሰማያዊው ፓርቲ አባሎቼ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየታሰሩብኝ ናቸው ሲል አማረረ።
የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢዴፓ/ በሀገሪቱ ለተፈጠሩ ችግሮች መፍትኄ ነው ያለውን እርቀ ሰላምና መግባባት ሊፈጥሩ የሚችሉ ተግባራትን የሚያከናውን ኮሚሽን እንዲቋቋም ጥሪ አቅርቧል፡፡
ለአለፉት ወራት በሃገሪቱ ውስጥ የተፈጠረው ቀውስና ሁከትም ሆነ በሕይወትና ንብረት ላይ ለደረሰው ጉዳት መሪውን ሚና የተጫወቱት ″የውጭ ኃይሎችና በሽብርተኝነት የተፈረጁት ኦነግ፣ እንዲሁም ግንቦት ሰባት ናቸው″ ሲሉ የኢፌዲሪ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ አስታወቁ።
ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) ዋና ተግባሩና መለያው በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩና መጮህና መጠየቅ ነው ሲል ገለፀ።
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራስያዊ አንድነት መድረክ በእሬቻ በዓል ላይ ለደረሰው ሕዝብ እልቂት ኃላፊነቱ የኢሕአዴግ መንግስት ነው አለ።
በኮንሶ አሁንም ዜጎች በጅምላ መታሰራቸው እንዲሁም የሰዎችና የቤተ ሃይማኖት ንብረቶች እየተዘረፉና እየተደፈሩ ናቸው ሲሉ የኮንሶን ህዝብ እንወክላለን ከሚሉ የኮሚቴ አባላት አንዱ ተናገሩ ፤የደቡብ ክልላዊ መንግስት ቃል አቀባይ ይህን አስተባብለዋል።
አንዲት አሜሪካዊት ቡራዩ አካባቢ በደረሰባቸው ጉዳት ሕይወታቸው ማለፉን አዲሰ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴት ኤምባሲ አሰታወቀ።
የትናንቱን የእሬቻ በዓል መደናቀፍና የተከሰተውን ጉዳት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ተቃውሞ መቀስቀሱን፣ የአንድ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ተናገሩ።
በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት የቁጫ ሕዝቦች ያነሱትን በቋንቋና በባህል እንዲሁም የራዝ ገዝ አስተዳድር ጥያቄ ተከትሎ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን፤ አንድ በዋስ ከእስር የተፈቱ ግለሰብ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ገለጹ።
ሰማያዊ ፓርቲ የጠራሁትን አስችኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ስላደናቀፈብኝ ኪሳራ አድርሶብኛል ሲል ቦርዱንም በህግ እንደሚጠይቅ የፓርቲው ኦዲት ኮሚሽን ያወጣው መግለጫ አስታወቀ።
በኮንሶ ሕዝቡን በማስገደድ ስብሰባ እየተካሄደ እንደሚገኝና ሕዝቡም ስብሰባውን እንዳልተቀበለው የኮንሶ ሕዝብ እንደወከላቸው ከሚናገሩ አባላት መካከል አንዱ አስታወቁ።
በመላው ሀገሪቱ የሰማያዊ ፓርቲ አባሎችና ሌሎችም ዜጎች ከሕግ ውጭ በሆነ አያያዝ በገፍ እየታሰሩ መሆናቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ተናገሩ።
ተጨማሪ ይጫኑ