በደቡብ ኢትዮጵያ በኮንሶ በተቀሰቀሰው ግጭት ጋር በተያያዘ ዛሬ አያሌ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር እየዋሉና ቤቶችም እየተፈተሹ መሆናቸውን ተነገረ።
በኮንሶ አንዳንድ ቀበሌዎች ተሠማርቶ የነበረው መከላከያ ሠራዊት ቢወጣም ከአከባቢው ወረዳዎች የተውጣጡ ታጣቂዎች ተተክተው በሁለት ቀበሌዎች እየተዋጉ ነው ሲሉ ከኮንሶ የሕዝብ ተወካዮች አንዱ ነኝ ያሉት አስታወቁ።
ከጳጉሜ 5, 2008 ዓ.ም. ምሽት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የመከላከያ ሰራዊት ኮንሶ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች ነዋሪዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን በጥቃቱም ቁጥሩ ያልታወቀ ሰው ሕይወት መጥፋቱን፤ በዞኑ ፖሊስ ጣቢያም የዐስራ አራት ሰው አስክሬን እንደሚገኝ እንደተናገራቸው ገልጸው በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ፣ ወደ 1000 ሺህ የሚጠጉ አባወራዎች ቀያቸውን ጥለው መጥፋታቸውን በሕዝብ እንደተመረጡ ከሚነገረው የኮሚቴ አባላት አንዱ አቶ ገመቹ ገንሴ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል። እሳቸው በተጨማሪ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው የደቡብ ክልል መንግሥት ነው ይላሉ።
ከጳጉሜ 5, 2008 ዓ.ም. ምሽት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የመከላከያ ሰራዊት ኮንሶ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ፍጽመዋል ሲሉ አንድ የሕዝብ ተወካይ ነኝ ያሉ ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቁ።
የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክርቤት ሰብሳቢ አቶ ይድነቃቸው ከበደ ትላንት መታሰራቸውንና ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን አንድ የፓርቲው አመራር አባል አስታወቁ።
በቂሊንጦ ማረምያ ቤት ከደረሰው ቃጠሎ በኃላ ለመጀመርያ ጊዜ በሕይወት ያሉ ታራሚዎች የት እንደሚገኙ መረጃ ተሰጠ።
ዛሬ ቅሊንጦ እስር ቤት የዘመዶቻቸውን ሁኔታ ለማጣራት የሄዱ የቤተሰብ አባላት ድብደባና እሥራት እንደተፈፀመባቸው ተናገሩ።
በቅዳሜው የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እሣት አደጋና ተኩስ የደረሰውን ጉዳት ማወቅ ባለመቻሉ “ቤተሰብ በእጅጉ ተጨንቋል” ሲሉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ፕሬዝዳንት ተናገሩ።
የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) የሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ዲሞክራሲያዊ መብት እንዲከበር አላስፈላጊ ያላቸው የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች የሀይል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀ።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ኢሕአዴግ ሲነሣ ከነበረበት ሁኔታ አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ የተለወጠ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ አስታውቀዋል፡፡
የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) የኢህአዲግ መንግሥት በአሁኑ ወቅት ከሕግ እና ከሥርዓት የወጣ የጉልበት እና የጭካኔ እርምጃ በጥብቅ አወግዛለሁ አለ።
በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ዛሬ ሰላማዊ ሰልፎችና እንቅስቃሴዎች እንደነበሩ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበ ለቪኦኤ ገለፁ፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በብሔራዊ ምክር ቤት የመተማመኛ ድምፅ የተነፈገው እንደ አንድ አካል ተሟልቶ ባለመሥራቱ እና የሥራ ቅደም ተከተል ስላልነበረው እንደሆነ የምክር ቤቱ ጠቅላላ ሰብሳቢ ገልጸዋል።
የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት በሥራ ላይ ላለው የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የመተማመኛ ድምፅ እንደነፈገው ታወቀ።
የዓለም ጤና ድርጅት ጉባዔ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።
የኢትዮጵያ ፈዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት( መድረክ) ሰሞኑን በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ደረሰ ላለው የዜጎች እልቂት ኃላፊነቱን የሚወስደው የኢህአዲግ መንግሥት ነው አለ።
የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አራቱን ከፍተኛ የአመራር አባላት ጨምሮ ዓቃቤ ህግ በሽብር ወንጀል ክሥ የመሠረተባቸው 22 ተከሳሾች ዛሬ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ