በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የነ አቶ ኃብታሙ አያሌው ጉዳይ እንደገና ተቀጠረ


ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የነ አቶ ኃብታሙ አያሌውና የነ ሶሊያና ሽመልስ ጉዳይ በመጓተቱ ጠበቃቸው ስሞታ አሰሙ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላት በነ አቶ ኃብታሙ አያሌው እንዲሁም በኢንተርኔት አምደኞቹ በነ ሶሊያና ሽመልስ እና በአቃቤ ህግ መካከል ባለው ክርክር ዛሬም ውሣኔ ሳይሰጥ ቀርቷል።

ለዚህ በምክንያትነት የቀረበው በችሎቱ የአዳዲስ ዳኞች መሰየም ነው።

ችሎቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ውሣኔው በመዘግየቱ ተከሳሾች ላይ ጉዳት ደርሷል ሲሉ የተከሳሾች ጠበቃ ቅሬታቸውን ገልፀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የነ አቶ ኃብታሙ አያሌው ጉዳይ እንደገና ተቀጠረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:26 0:00

XS
SM
MD
LG