ለዲቪ ሎተሪ የሚያመለክቱ ወይንም ያመለከቱ ኢትዮጵያውያን ራሣቸውን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቁ በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አስጠነቀቀ፡፡
የፆታ እኩልነትን የልጃገረዶችንና የወጣት ሴቶችን መብት ለማስጠበቅ በሚደረገው እንቅስቃሴ የአፍሪካ መንግሥታት ከፖለቲካ ፈቃደኝነታቸው ጋር የሚመጣጠን፣ ሃብት እንደማይመድቡ ተጠቆሙ፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት አራት የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ከፍተኛ አመራር አባላትን ጨምሮ በሃያ ሁለት ተከሳሾችና በዓቃቤ ሕግ መካከል ባለው ክርክር ላይ ዛሬም ብይን ሳይሰጥ ቀረ፡፡ ተከሳሶቹ ፍርድ ቤት አለቀረቡም፡፡
በአለፉት ጥቂት ዓመታት በአፍሪካ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ በአሥር በመቶ የቀነሰ ቢሆንም የግዳጅ ሥራንና የህፃናት ጉልበት ብዝበዛን ለመቀነስ ብሎም ለማጥፋት ከፍተኛ ድካም ይጠይቃል ሲሉ የኢትዮጵያው የሠራተኛና የማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር አስታወቁ፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የዶ/ር መረራ ጉዲና ጠበቆች ያቀረቡት ተጨማሪ መቃወሚያ የወንጀል ሕግ ስነሥርዓቱን ድንጋጌዎች ያልተከተለ ነው አለ፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል ተከሰው ሲከራከሩ ከቆዩ አሥራ ሦስት ተከሳሾች መካከል ስድሥቱን በነፃ ሲያሰናብት በሰባቱ ላይ ጥፋተኞች ሲል ፈረደ፡፡
"የአፋን ኦሮሞ ፊደል /ቁቤ/ ቅደም ተከተል ተለውጧል መባሉ እውነት አይደለም" ሲሉ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ባለሥልጣን ተናገሩ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ረጲ አካባቢ በተለምዶ “ቆሼ” በተባለው ሥፍራ ከጥቂት ወራት በፊት ከቆሻሻ ክምር መናድ ሳቢያ የሞቱት ዜጎች ቁጥር አንድ መቶ አሥራ አምስት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
የ1997 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ምርጫ ተክትሎ በተከሰተው ቀውስ ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም. በመንግሥት ታጣቂዎች የተገደሉ ዜጎች አሥራ ሁለተኛ ዓመት መታሰቢያ ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፅ/ቤት ተከበረ፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት በዓቃቤ ሕግና አራት የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ የአመራር አባላትን ጨምሮ በሃያ ሁለት ተከሳሾች መካከል ባለው ክርክር ላይ ዛሬም ብይን ሳያሰማ ቀረ፡፡
የኢንተርኔት አገልግሎት የተዘጋው የተፈታኝ ተማሪዎችን ጥቅም ለመጠበቅ ነው ሲል የመንግሥት ኮምየኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት አሥራ ዘጠነኛ ወንጀል ችሎት ዓቃቢ ሕግ በዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ ያቀረበውን ክስ እንዲያሻሽል ትዛዝ ሰጠ፡፡
በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኋላ በአሥራ ዘጠኝ ሰዎች ላይ ሕገ ወጥ ግድያ እንደተፈፀመ፣ ከሃያ ሺሕ በላይ ሰው መታሠሩንና በብዙዎች ላይ በማሰቃየት ምርመራ እንደተካሄደባቸው የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ(ሰመጉ) አስታወቀ፡፡
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና በጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ላይ ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት በማደረግና የተለያዩ የሽብርተኛ ድርጅቶችን ሃሳብ የሚገልፁ ፁሑፎችን እንዲሁም ምስሎችን ይዛችሁ ተገኝታችኋል በሚል የወንጀል ክስ መሰረተባቸው፡፡
“ነገረ ኢትዮጵያ” ተብሎ የሚታወቀውን የሰማያዊ ፓርቲ ልሣን አዘጋጅ በነበረው ጌታቸው ሽፈራው ላይ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት የአንድ ዓመት ከሥድስት ወር የእስር ጥቃት ወሰነበት፡፡
የፌደራሉ ከፈተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በነበረው ዮናታን ተስፋዬ የስድስት ዓመት ከስድስት ወር የእስር ቅጣት ጣለበት፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሥራ ዘጠነኛ ወንጀል ችሎት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎና በሌሎች ወንጀሎች ክስ የተመሰረተባቸው ሠላሳ ስምንት ተከሳሾች ጉዳይ በዝግ ችሎት እንዲታይ የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቢ ሕግ ባቀርበው ጥያቄ ዛሬም ብይን አልሰጠም፡፡
የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ እና ሰማያዊ ፓርቲ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ አባሎቻቸውን ለመጎብኘት እንደተከለከሉ ተናገሩ፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ክፍል የቀድሞ ኃላፊ ዮናታን ተስፋዬ በተከሰሰበት የሽብር ወንጀል የጥፋተኛነት ብይን ተላለፈበት፡፡
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ አራት ከፍተኛ የአመራር አባላትን ጨምሮ በሃያ ሁለት ተከሳሾችና በዐቃቤ ህግ መካከል ባለው ክርክር ላይ ዛሬ ሊሰጥ የነበረው ብይን እንዳልደረሰለት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት አስታወቀ፡፡ ችሎቱ ተለዋጭ ቀጠሮም ሰጥቷል።
ተጨማሪ ይጫኑ