አዲስ አበባ —
ለዲቪ ሎተሪ የሚያመለክቱ ወይንም ያመለከቱ ኢትዮጵያውያን ራሣቸውን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቁ በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አስጠነቀቀ፡፡
ዲቪ ወይንም ዳይቨርስቲ ቪዛ የተባለውን ወደ አሜሪካ ሀገር ሊያስገባ የሚችል ቪዛን ለመስጠት የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ማንንም አልወከለም ሲሉ አንድ የኤምባሲው ባለሥልጣን አስታወቁ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ከዓለም የተለያዩ ሀገሮች ዜጎች ዳይቨርስቲ ቪዛ (ዲቪ ሎተሪ) በመጠቀም ወደ ግዛቱ እንዲፈልሱ ማድረግ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡
ከኢትዮጵያም በየዓመቱ ከ4 እስከ 6 ሺሕ የሚሆኑ የዲቪ አመልካቾች እንዳሉ ያስታወሱት በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የማጭበርበር ተግባራት መከላከያ ክፍል ሥራ አስኪያጅ ቶማስ ቤልስ ወደ አሜሪካ ለመፍለስ ብዙ ፍላጎት እንዳለ አመልክተዋል፡፡
ይሔን ከፍተኛ ፍላጎት በመመልከትም ከዚህ ጥቅም ለማግኘት የሚጥሩ አካላት እንዳሉ ማወቅ ተችሏል ብለዋል፡፡ በዚህ ምክንያት የተለያዩ የማጭበርበር ተግባራት ሲፈፀሙ እናስተውላለን ይላሉ፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ