አዲስ አበባ —
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል ተከሰው ሲከራከሩ ከቆዩ አሥራ ሦስት ተከሳሾች መካከል ስድሥቱን በነፃ ሲያሰናብት በሰባቱ ላይ ጥፋተኞች ሲል ፈረደ፡፡
በነፃ የተሰናበቱት ዛሬውኑ ከወይሕኒ እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
የቅጣት ውሳኔውን ለማሰማትም ቀጠሮ ቆርጧል፡፡ በሌላ መዝገብ ደግሞ በነጉርሜሳ አያኖ ጉዳይ ብይኑን ለማሰማት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ