አዲስ አበባ —
በአለፉት ጥቂት ዓመታት በአፍሪካ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ በአሥር በመቶ የቀነሰ ቢሆንም የግዳጅ ሥራንና የህፃናት ጉልበት ብዝበዛን ለመቀነስ እና ለማጥፋት ከፍተኛ ድካም ይጠይቃል ሲሉ የኢትዮጵያው የሠራተኛና የማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር አስታወቁ፡፡ በኢትዮጵያም ችግሩ ሙሉ በሙሉ አልተቀረፈም ብለዋል፡፡
ከሠሃራ በስተደቡብ የሚገኙ የአፍሪካ ሀገሮች የህፃናትን ጉልበት ብዝበዛ እና የግዳጅ ሥራን በተመለከተ ለሁለት ቀናት የሚቆይ የምክክር መድረክ ዛሬ እረፋዱ ላይ በአዲስ አበባ ኢሌሌ ሆቴል ተከፍቷል፡፡ በዚህ የምክክር መድረክ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ መንግሥት የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ አብዱል ፈታህ አብዱላሂ የዓለም የሥራ ድርጅትን /አይ ኤል ኦ/ን መረጃዎች በመጥቀስ በአፍሪካ ውስጥ 3.7 ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶች፣ ወንዶችና ህፃናት የግዳጅ ሥራና የጉልበት ሥራ ብዝበዛ ሰለባዎች ናቸው ብለዋል፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ