ዓለም አቀፉ የውሃ ኃይል ጉባዔ በአፍሪካ አህጉር የመጀመሪያ ጉባዔውን እያካሄደ ነው፡፡
ደራሲ፣ ዲፕሎማት፣ አርበኛ፣ መምህር የክብር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ ከነኀስ የተሠራ ኃውልት ቆመላቸው፡፡
“የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገሪቱ መፃኢ ዕድል በእጁ ነው” ሲሉ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከፍተኛ ኮሚሺነር አስገነዘቡ፡፡
የጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ መንግሥት በድርቅ ለተጎዱ የአፍሪካ ሀገሮች የሚሠጠውን ዕርዳታ ወደ 1.5 ቢሊዮን ዩሮ ከፍ እንደሚያደርግ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝም ሆነ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሽግግር ላይ የሚገኝ በመሆኑ ጉድለቶች እንዳሉት ጠ/ሚ ኃይለማሪያን ደሳለኝ አስታወቁ፡፡
የተለያዩ ዕቃዎችን እና ቁሳቁስ ገዝቶ ወደ ሃገር በማስገባት ብቻ ሀገርን ማሳደግ፣ ብሎም ማበለፀግ አይቻልም ሲሉ የኢትዮጵያው የሣይንስና የቴክኖሎጂ ሚኒስትር አስገነዘቡ፡፡
የዶ/ር መረራ ጉዲና ጠበቆች የፌደራሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ለመሰረተባቸው ክስ መቃዎሚያቸውን በፅሑፍ አቀረቡ፡፡
አሚሶም በመጭው ዓመት "ከሶማልያ ይወጣል"
በኢትዮ - አሜሪካን ዶክተርስ ሜዲካል ሲቲ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ወጭ ለሚገነባው ሆስፒታል ጠ/ሚኒስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝ የመሠረት ድንጋይ አኖሩ፡፡
አንዳንድ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በሽብር ወንጀልና በሌሎች ዓይነት ወንጀሎች ተጠርጥረው እየተጠየቁ መሆናቸውን የፓርቲው ሊቀመንበር ተናገሩ፡፡
ከሰኔ 2008 ዓ.ም. እስከ መስከረም መጨረሻ 2009 ዓ.ም. በነበሩት ወራት በኦሮሚያ፣ በአማራና በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች ክልሎች ተፈጥረዋል ባላቸው ሁከትና ብጥብጥ «የስድሥት መቶ ስድሣ ዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል» ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
የፋሲካ ገበያ በአንዳንድ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ ማምጣቱን ነጋዴውም ሆነ ሸማቹ ይስማማል፡፡
ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ዓለም አቀፉ የሰው ልጆች ብልፅግና ወይንም ልማት ዕድገት ምጣኔ በከፍተኛ ፍጥነት ቢገሰግስም ከሠሃራ በስተ ደቡብ ያሉ የአፍሪካ ሀገሮች ግን እኩል ተጠቃሚ እንዳልነበሩ ዓመታዊው የሰው ልጅ ብልፅግና ወይንም ልማት ዘገባ አመለከተ፡፡
ዓቃቤ ሕግ በእነ አቶ በቀለ ገርባ ላይ ያቀረበውን የድምፅ ከምስል ማስረጃ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዛሬም እንዳልተረጎመው አስታወቀ። አቶ በቀለ ገርባ ከዚህ በኋላ በኃይል ተገድጄ ካልሆነ ችሎት አልቀርብም አሉ።
ዓቃቤ ሕግ በእነ አቶ በቀለ ገርባ ላይ ያቀረበውን የድምፅ ከምስል ማስረጃ ዛሬም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በፍርድ ቤቱ የሥራ ቋንቋ እንዳልተተረጎመ ታወቀ፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በኢንተርኔት አምደኞቹ በነ ሶሊያና ሽመልስና በዓቃቤ ሕግ መካከል ባለው ክርክር ዛሬ ውሳኔ ሰጠ፡፡
መላው የኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ እና ሰማያዊ ፓርቲ አብሮ የመሥራት ስምምነት ሠነድ ተፈራረሙ፡፡ የሁለቱ ፓርቲዎች መሪዎች ይሕ ትብብራቸው ሰፋ ባለ ጥናት ላይ የተመሠረተ እንደሆነና ወደ ውሕደት የሚዘልቅ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮጵያን በይፋ በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ኤርትራን በመጨመር አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሠብ ለመፍጠር መስራት አለባቸው አሉ፡፡
የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ዛሬ የመጨረሻ የመከላከያ ማስረጃውን ለፍርድ ቤት አቀረበ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ