አዲስ አበባ —
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት በዓቃቤ ሕግና አራት የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ የአመራር አባላትን ጨምሮ በሃያ ሁለት ተከሳሾች መካከል ባለው ክርክር ላይ ዛሬም ብይን ሳያሰማ ቀረ፡፡ ተከሳሾች ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ የአመራር አባላት አቶ ጉርሜሳ አያኖ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ አዲሱ ቡላላ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በሃያ ሁለት ተከሳሾችና በዓቃቤ ሕግ መካከል ባለው ክርክር ላይ ፍርድ ቤቱ ዛሬ ብይን እንደሚሰጥ ሲጠበቅ የቆየ ቢሆንም ብይኑ እንዳልደረሰለት አስታውቋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ