አዲስ አበባ —
በአዲስ አበባ ከተማ ረጲ አካባቢ በተለምዶ “ቆሼ” በተባለው ሥፍራ ከጥቂት ወራት በፊት ከቆሻሻ ክምር መናድ ሳቢያ የሞቱት ዜጎች ቁጥር አንድ መቶ አሥራ አምስት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
የከተማው አስተዳደር ይፋ ባደረገው መግለጫ ለተለያዩ ጉዳቶች ተጋልጠዋል ያላቸውን በተጣራ መረጃ መያዙን ይናገራል፡፡ እስከ ትናንት በስቲያ ለጉዳተኞቹ የተሰበሰብው ገንዘብ ከ94 ሚሊዮን ብር በላይ ደርሷል፡፡
የአደጋው መንስዔ አሁንም እየተጠና መሆኑ ተገልጧል፡፡
አንዳንድ የጉዳቱ ሰለባዎች ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ