አዲስ አበባ —
የኢንተርኔት አገልግሎት የተዘጋው የተፈታኝ ተማሪዎችን ጥቅም ለመጠበቅ ነው ሲል የመንግሥት ኮምየኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
እርምጃውን «በትክክል የሚያስብ ዜጋና ተጠያቂነት ያለው መንግሥት የሚያደርገው ነው» ብለዋል፤ የፅሕፈት ቤቱ ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ለውጭ መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ፡፡
በሃገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተውን ድርቅ መንግሥት ሊቋቋመው እንደሚችልም ዶ/ር ነገሪ ተናግረዋል፡፡
ሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች እየተመለሱ እንደሆኑም ገልፀዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ