በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መርማሪዎችና ጋዜጠኞች ወደ አማራ ክልል እንዲገቡ ተጠየቀ


ፍኖተ ሰላም ከተማ
ፍኖተ ሰላም ከተማ

አማራ ክልል ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከተጣለ ወዲህ ተፈፅመዋል የተባሉ የመብት ጥሰቶችን መርመር እንዲቻል ባለሥልጣናቱ ለገለልተኛ መርማሪዎችና ለመገናኛ ብዙኃን ያልተገደበ ፍቃድ በአፋጣኝ እንዲሰጡ ዓለምአቀፉ የመብቶች ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።

ክልሉ ውስጥ በኢትዮጵያ ብሄራዊ የመከላከያ ኃይልና በታጠቁ የፋኖ ሚሊሽያ መካከል እየተካሄደ ባለው ውጊያ መሃል “ብርቱ” ያላቸው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈፀሙ መሆናቸውን የሚጠቁሙ ሪፖርቶች እየደረሱት መሆኑን ቡድኑ ዛሬ፤ ዓርብ ባወጣውና ዌብሳይቱ ላይ ባሠፈረው ፅሁፍ አስታውቋል።

በክልሉ ውስጥ በዚህ ሣምንት የአየር ድብደባ መፈፀሙንና ብዙ ሲቪሎች መገደላቸውን፤ ፍኖተ ሰላም፣ ባህር ዳርና ሸዋ ሮቢት ውስጥ መደዳ ግድያ መፈጸሙንና የሰፋ ጉዳት መድረሱን መገናኛ ብዙኃን መዘገባቸውን ያመለከተው አምነስቲ ኢንተርናሽናል “ሁኔታው ምርመራ ሊደረግበት የሚገባ ነው” ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ አስተያየት የሰጡት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ታይገሪ ቻጉታ "አማራ ክልል ውስጥ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈፀሙ መሆናቸውን የሚናገሩ አቤቱታዎችን ተከትሎ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የተቋቋመው በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ባለሙያዎች ኮሚሽንና ሌሎችም ገለልተኛ መርማሪዎች፣ እንዲሁም ነፃ መገናኛ ብዙኃን በጥልቀት መመርመር እንዲችሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ያልተገደበ ፍቃድ መስጠት አለበት" ማለታቸውን የቡድኑ ፅሁፍ ጠቁሟል።

"መንግሥትና የፀጥታ ኃይሎቹ ሰብዓዊ መብቶችን ማክበር እና መጠበቅ አለባቸው"

ዳይሬክተሩ አክለውም "መንግሥትና የፀጥታ ኃይሎቹ ሰብዓዊ መብቶችን ማክበር እና መጠበቅ አለባቸው" ብለዋል።

ባለፈው ሃምሌ 28/2015 ዓ.ም. የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመንግሥቱ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ አቅም የሚሰጠው እንደሆነ የጠቆሙት ቻጉታ "አሁን ጊዜው ዓለምአቀፍና አህጉራዊ አካላት በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ክትትል የሚያላሉበት አይደለም” ማለታቸውን የአምነስቲ ፅሁፍ አመልክቷል።

ባለፈው ሣምንት ማክሰኞ፤ ነሃሴ 2 በፓርላማው የፀደቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መንግሥት ተጠርጣሪዎችን ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የመያዝ፣ የሰዓት እላፊ ገደብ የመጣል፣ ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብትንና የመሰብሰብ ነፃነትን የመገደብ ሰፊ ሥልጣን የሚሰጥ ነው።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተጨማሪም ክልሉን በሃገሪቱ የደኅንነት ጉዳዮች ኃላፊ በሚመራው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጥታ ተጠሪ በሚያደርገው የአስቸኳይ ጊዜው ማዘዣ ማዕከል ሥር እንዲውል የሚያደርግ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውሷል።

ለዚህ የዛሬ የአምነስቲ መልዕክት የኢትዮጵያን መንግሥት ምላሽ ለማግኘት ያደርነው ተደጋጋሚ ጥረት ለዛሬ አልተሳካም። ይሁን እንጂ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ባለፈው ሣምንት ዐርብ በሰጡት መግለጫ “መንግሥት ማንኛውንም ጥቃት መከላከል የሚያስችል ኃይል አስታውቀው “የአማራ ክልል ግጭት በሰላም እንዲፈታ ከተፈለገ ግን ‘ፅንፈኛና ዘራፊ’ -- ያሉት አካል -- “ትጥቅ ፈትቶ ወደተዘጋጁለት ካምፖች መግባት ይኖርበታል” ማለታቸው ተዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG