በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ቅዳሜ 25 ጥር 2020

Dr. Dawd Seid Siraj

“አደንጋጭ ከሆኑት የኮሮናቫይረስ ይሄ ሶስተኛው ነው። በተፈጥሮው ከአእዋፋት ወደ ሰው የሚተላለፍ ቫይረስ አደገኛ የሚሆነው ከሰው ወደ ሰው መተላለፍ ሲጀምር ነው። አሁን ከዚያ የደረሰ ይመስላል። አሳሳቢ ያደረገውም ያ ነው።” ዶ/ር ዳውድ ሰይድ ሲራጅ በዊስኮንሰን ዩኒቨርሲቲ የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና ክፍል ፕሮፌሰር።

በእንግሊዝኛው አጠራሩ Coronavirus ይባላል።

አዲስና በፍጥነት በመዛመት ላይ መሆኑ የተነገረለትን የዚህን ወረርሽኝ ምንነት፣ መንስኤ፣ የመተላለፊያ መንገዶች እና ወረርሽኙ ወደተከሰተበት አካባቢ የሚደረግ ጉዞም ሆነ ከዚያ የሚመጡ ሰዎች ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥያቄዎችና ሥጋቶች ይመረምራል።

ሞያዊ ማብራሪያውን የሚሰጡን ዶ/ር ዳውድ ሰይድ ሲራጅ በዊስኮንሰን ዩኒቨርሲቲ የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና ክፍል ፕሮፌሰር እና ከዓለም አቀፍ ጉዞ ጋር የተዛመዱ የሕክምና ጉዳዮች ክትትል ክፍል ዲሬክተርም ናቸው።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ማወቅ ያለብዎ፡- በፍጥነት በመዛመት ላይ ያለ አዲስ ወረሽኝ ከወደ ቻይና
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:51 0:00


ከቻይና ጋር በንግድና ሌሎችም የምጣኔ ኃብት መስኮች የተሳሰረቸ ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መዛመት ጉዳይ ከሚያሳስባቸው ሀገሮች አንዷ እንደሆነች እየተነገረ ነው።

የማኅበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ ለመንገደኞች ሰለቫይረሱና ስለሚተላለፍባቸው መንገዶች መረጃ እንደሚሰጥና በዓለም የጤና ድርጅት ምክር መሰረትም ቦሌ ዓለምቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ላይ የሰውነት የሙቀት መጠን ምርመራ ማድረግ መጀመሩን አስታውቋል።

ቫይረሱና የሚያስከትለውም ህመም ወደታየባቸው አካባቢዎች የሚጓዙ መንገደኞች፣ የሳልና የትኩሳት ምልክት ከሚታይባቸው ሰዎች እንዲርቁ፣ በአመጋገብና በግል ንፅህና አጠባበቅ ላይም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ፣ የኢትዮውያን የመከላከልና የዝግጅነት ሥራ የሚያስተባብረው የማኅበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መክሯል።

የዓለም የጤና ድርጅትም ትናንት በሰጠው መግለጫ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምቀፍ ሥጋት መደቀኑን አስታውቋል። ይሁን እንጂ ከቻይና ውጭ የጤና አደጋ ነው ብሎግን አላወጀም።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኮረናቫይረስ ሥጋት አይሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:22 0:00


ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG