በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐማራ ክልል ዋና ዋና ከተሞች የተኩስ ድምፅ ሳይሰማ እንደዋለ ነዋሪዎች ተናገሩ


በዐማራ ክልል ዋና ዋና ከተሞች የተኩስ ድምፅ ሳይሰማ እንደዋለ ነዋሪዎች ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:17 0:00

በዐማራ ክልል ዋና ዋና ከተሞች የተኩስ ድምፅ ሳይሰማ እንደዋለ ነዋሪዎች ተናገሩ

ከባሕር ዳር፣ ጎንደር እና ሸዋሮቢት ከተሞች፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች፣ በዛሬው ውሎ የተኩስ ድምፅ እንደማይሰማና በከተሞቹ የመከላከያ ሠራዊት አባላት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

በትላንትናው ዕለት በግድያ ሕይወታቸው እንዳለፈ የገለጿቸውና በአብዛኛው ሰላማዊ ናቸው ያሏቸው ሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዐትም እየተፈጸመ እንደኾነም ተናግረዋል፡፡ ከተለያዩ ግልጋሎቶች መቋረጥ ጋራ ተያይዞ፣ ማኅበረሰቡ እየተቸገረ እንደሚገኝም፣ አስተያየት ሰጪዎቹ አክለው ገልጸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ባወጣው መግለጫ፣ “የባሕር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን፣ ላሊበላ፣ ጎንደር እና ሸዋ ሮቢት ከተሞች፥ ከዘራፊው መንጋ ስጋት ነፃ ኾነዋል፤” ብሏል፡፡

የጠቅላይ መምሪያ ዕዙ፣ “ነፃ ኾነዋል” ባላቸው ከተሞች፣ ከነገ ጀምሮ፣ የአውሮፕላን በረራ እና ሌሎች አገልግሎቶችም እንደሚጀመሩ ጠቁሟል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ፣ ወደ ባሕር ዳር እና ጎንደር ከተሞች፣ በነገው ዕለት በረራ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG