በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግሥትን የተቃወመው ሰልፍ - በዋሽንግተን ዲሲ


የኢትዮጵያ መንግሥትን የተቃወመው ሰልፍ - በዋሽንግተን ዲሲ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:29 0:00

የኢትዮጵያ መንግሥትን የተቃወመው ሰልፍ - በዋሽንግተን ዲሲ

በዐማራ ሕዝብ ላይ፣ ለዓመታት ማንነትን የለየ በደል ተፈጽሞበታል፤ ያሉ ኢትዮጵያውያን፣ ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ፣ ሰልፍ አካሔዱ። የሰልፉ አስተባባሪዎች፣ “የኅልውና አደጋ ተጋርጦበታል” የተባለውን ሕዝብ የመከላከል ዓላማ አለው፤ ላሉት፣ የዐማራ ሕዝባዊ ሠራዊት-ፋኖ ድጋፋቸውን አሰምተዋል።

በሌላ በኩል፣ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ባለፈው ዐርብ በዐማራ ክልል ላይ ለአወጣው፣ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ አፈጻጸም ያቋቋመው፣ የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ፣ በክልሉ የሚንቀሳቀሰውን የፋኖ ታጣቂ፣ “ዘራፊ እና ጽንፈኛ መንጋ ነው፤” ብሎታል።

የዛሬ የዋሽንግተን ዲሲ ሰልፈኞች በበኩላቸው፣ በዐማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ነው፤ ያሉትን ግፍ በትጥቃዊ ትግል ለመመከት፣ የፋኖ ታጣቂ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ፣ ሌላ ስም በመስጠት፣ ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋራ ለማራራቅ የሚደረገው ጥረት፣ ሊቆም እንደሚገባ አሳስበዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG