በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐማራ ሕዝብ ላይ የተፈጸሙ ተደራራቢ መንግሥታዊ በደሎች ለትጥቃዊ ግጭቱ ዋና መነሻ እንደኾነ የጎንደር ፋኖ አመራሩ ተናገሩ


በዐማራ ሕዝብ ላይ የተፈጸሙ ተደራራቢ መንግሥታዊ በደሎች ለትጥቃዊ ግጭቱ ዋና መነሻ እንደኾነ የጎንደር ፋኖ አመራሩ ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:37 0:00

በዐማራ ሕዝብ ላይ የተፈጸሙ ተደራራቢ መንግሥታዊ በደሎች ለትጥቃዊ ግጭቱ ዋና መነሻ እንደኾነ የጎንደር ፋኖ አመራሩ ተናገሩ

  • የክልሉን ሰላም ያደፈረሱት “የተደራጁ ዘራፊ ቡድኖች” እንደኾኑ አቶ ተመስገን ተናገሩ

የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዲሬክተር ጀነራል እና የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ዋና ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ ለመንግሥታዊ ብዙኀን መገናኛ በሰጡት ማብራሪያ፣ “የተደራጁ ዘራፊ ቡድኖች” ባሏቸው አካላት፣ በክልሉ የተከሠተው የሰላም መደፍረስ፥ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና አስተዳደራዊ ችግሮችን መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል፣ የክልሉን መንግሥት እና የፌዴራሉን መንግሥት መዋቅሮች እና ኃይሎች፣ በጠመንጃ ለመነቅነቅ እየሞከሩ ነው፤ በሚል ወቀሳ ከሚቀርብባቸው የክልሉ ውስጥ ተፋላሚዎች ዋናው፣ “ፋኖ” በሚል የሚጠራው አደረጃጀት ነው።

በተለያዩ የክልሉ ሥፍራዎች እንደሚገኙ ከሚነገርላቸው የፋኖ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ፣ የጎንደር እና አካባቢ ትግልን እንደሚያስተባብር የሚናገረው አደረጃጀት ይገኝበታል። በአደረጃጀቱ ውስጥ በአመራርነት እያገለገሉ እንደሚገኙ የተናገሩ ግለሰብ፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ባደረጉት ቆይታ፣ በክልሉ እና በፌዴራል መንግሥቱ ባለሥልጣናት በኩል ስለሚቀርቡ ውንጀላዎች እና ትጥቃዊ ግጭቶች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እኒኹ አመራር፣ በክልሉ ሕዝብ ላይ በተደጋጋሚ የተፈጸሙ በደሎች፣ አሁን ላይ በግልጽ ለታየው የትጥቅ መገዳዳር ምክንያት እንደኾነ በአጽንዖት አውስተዋል፡፡ ችግሩን ለማረም እና የተበደለውን ሕዝብ ለመካስ፣ መንግሥት ጥፋቱን አምኖ፣ ተጠያቂዎችን ለሕግ ማቅረብ፣ ከአስፈላጊ ርምጃዎች አንዱ እንደኾነ ተናግረዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG