በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግጭት በከፋበት የዐማራ ክልል አካባቢ ርዳታ እንዲቀርብ ሕፃናት አድን ድርጅት ተማፀነ


ፎቶ ፋይል፦ ባሕር ዳር ከተማ
ፎቶ ፋይል፦ ባሕር ዳር ከተማ

የግጭት መባባስን ተከትሎ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ በታወጀበት በዐማራ ክልል፣ የሰብአዊ ርዳታ ተደራሽነት እንዲቀጥል ይደረግ ዘንድ፣ ሕፃናት አድን ድርጅት፣ ዛሬ ረቡዕ ተማፅኖ አቀረበ።

በኢትዮጵያ የሕፃናት አድን ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ዜቪዬር ዡቤር፣ ዐማራ ክልል በአሳሳቢ ኹኔታ የተባባሰው ግጭት፣ ሕፃናትን ጨምሮ ቤተሰቦችን ለአደጋ እያጋለጠ እንደኾነ ተናግረዋል፡፡

“የቅርብ ጊዜው[የሰሜን ኢትዮጵያ] ጦርነት ቁስል ሳይደርቅ፣ የሕፃናት ሕይወት ለአደጋ እየተጋለጠ ነው፡፡ እኛ፣ እንደ የሰብአዊ ርዳታ ድርጅት፥ ተዋጊ ወገኖች፣ ለሲቪሎች ደኅንነት ቅድሚያ እንዲሰጡ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ በቀደመው ግጭት የተፈናቀሉትን 580 ሺሕ ሰዎች ጨምሮ፣ ችግር ላይ ላሉት በሙሉ፣ ሰብአዊ ረድኤት ማቅረብ እንዲቻል እንማፀናለን፤” ብለዋል፡፡

ሕፃናትን፥ ከሁከት፣ ከመፈናቀል፣ ከረኀብ፣ ከሠቆቃ መጠበቅ ይኖርብናል፤ ያሉት የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ፣ ለአደጋ የተጋለጡ ቤተሰቦች፣ ጥበቃ ሊያገኙና መሠረታዊ ሰብአዊ ርዳታ ሊቀርብላቸው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG