የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) በበኩሉ ሠራዊቱ በእንደዚህ ዓይነት ተግባር ላይ እንደማይሰማራ አስታውቋል።
በቡራዩና አካባቢው የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 58 መሆኑን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እስካሁን ከየሆስፒታሉ የተሰበሰበው መረጃ በእጃቸው እንዳልደረሰ ገልጾ ቁጥሩ አምነስቲ የጠቀሰው ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።
የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኅብረተሰቡ በማኅበራዊ ድረ ገፅ በሚለቀቁ ስጋት ፈጣሪ ሐሳቦች ተነሳስቶ ግጭት ውስጥ እንዳይገባ አሳሰበ። በከተማዋ ግጭት ለመፍጠር የሚፈልግ አካል ካለም ፖሊስ የማይታገስ መሆኑን አውቆ ከጥፋት ድርጊት እንዲታቀብ አሳስቧል። የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ሕዝብ ግንኝነት ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ሳጅን ባንታለምን አነጋግረናቸዋል።
አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በባንዲራ ጉዳይ ትናንትና ዛሬ ግጭት መፈጠሩን ነዋሪዎችና ፖሊስ አስታወቀ።
በኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ የተናቃዮች ቁጥር በሶርያ ከተመዘገበው እንደሚልቅ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ተከታትሎ የሚመዘግብ (IDMC) የተባለ ዓለም አቀፍ ተቋም አስታወቀ።
ሕዝብን ማዕከል ያደረገ ትስስር በመፍጠር የሀገሪቱን የኢኮኖሚ አቅም መገንባት እንደሚቻል ዶ/ር አክሎግ ቢራራ ጥቆማ አቀረቡ።
የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች ለዓመታት ከፍተኛ ሙቀት ባለበት ምሽግ ውስጥ በአሳዛኝ ሁኔታ ተቀምጠው እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለፁ።
አዲስ ዓመትን ምክኒያት በማድረግ እስረኞች ከአራት ክልሎች በይቅርታ መለቀቃቸውን የክልል ባለሥልጣናት አስታወቁ። በሌላ በኩል በሽብር ወንጀል ተከሰው እስከዛሬ ያልተፈቱ እስረኞች በፌደራል ማረሚያ ቤቶች እንደሚገኙ ጠበቆችና ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሶማሊያና የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጅቡቲ ተገናኝተው በጋራ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ።
በሥራ ማቆም አድማ ላይ የነበሩትና በኋላም ለእስር የተዳረጉት የኢትዮጵያ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጥያቄ የደሞዝ ጭማሪና የሞያ ማረጋገጫ እውቅን የሚጠይቁ የመብት ጥያቄዎች ናቸው ሲሉ በውጭ ሀገር የሚገኙ የቀድሞ ሠራተኞች ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።
በኢትዮጵያ በሶማሌና በኦሮሚያ አዋሳኝ ክልል ላይ በተፈጠረ የጎሳ ግጭት ስምንት ሰው መሞቱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ተቃውሞን በማሰማት፣ ትችት በመሰንዘርና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ጉዳይ ይዞ አደባባይ በመውጣት የሚታወቀው አርቲስት ታማኝ በየነ ከ22 ዓመታት በኋላ በመጪው ቅዳሜ ኢትዮጵያ ሊገባ መሆኑን አስታወቀ። የአርቲስት ታማኝ አቀባበል የኢትዮጵያዊያን አንድነት ማብሰሪያ ምልክት እንደሚሆን አዲስ አበባ የሚገኘው የአቀባበሉን መርሃ ግብር የሚመራው ኮሚቴ አስታውቋል።
የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመርና ሌሎች ስድስት የክልሉ ምክር ቤት አባላት በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ። ኮሚሽነሩ ሐምሌ 27/2010 ዓ.ም በቀድሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት አመራር ሰጪነት በተቀነባበረ ወንጀል የ96 ሰው ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል።
የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባላትና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አመራሮችና አባላት አዲስ አበባ ከሚገኙት የዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ እንደራሴ አባላት ጋር ተወያዩ። ለምክር ቤቱ አባላት ባለፉት 27 ዓመታት በአማራ ሕዝብ ላይ ደረሰ ያሉትን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ በደሎችና መገፍፋትን ማስረዳታቸውን አመራሮቹ ለአሚሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም በሞባይልና በኢንተርኔት አገልግሎቶች ላይ ከ40 በመቶ በላይ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ።
በሶማሌ ክልል በዋና ከተማው ጂግጂጋን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች የተፈፀመው ጥቃት እጅግ ዘግናኝ እንደነበር ከከፍተኛ ድብደባ በኋላ በሕክምና የተረፉት የኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ገለፁ። በኢትዮጵያ ሶማሌ ሀገረስብከት በጂጂጋ ምስራቀፀሐይ ኪዳነምሕረት ካቴድራል አስተዳዳሪ መላከፀሐይ አባገብረፃዲቅ ደባብን አነጋግረናቸዋል።
ዐሥራ አምስት አባላት ያሉት የዴያስፖራ ትረስት ፈንድ አማካሪ ምክር ቤት አባላት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ጥሪ ተቀብለው በበጎ ፈቃደኝነት ለማገልገል የተሰባሰቡ እንደሆኑ የአማካሪ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማሪያም አስታወቁ።
በሶማሌ ክልል ጂጂጋ ከተማ የተፈጠረውን ግጭት ለማረጋጋት በክልሉ የተለያዩ ከተሞች የመከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ከገቡ በኋላ የነበሩት ጥቃቶች ቆመው አንፃራዊ መረጋጋት ቢኖርም ከፍተኛ የሆነ የምግብና የመጠጥ ችግር መከሰቱን ነዋሪዎች ገለፁ።
ከቅዳሜ ጀምሮ በውጥረት ውስጥ ወደ ሰነበተችው ሶማሌ ክልል ጂጂጋ ከተማ ማምሻውን የመከላከያ ሠራዊት በመግባቱ ከተማው እየተረጋጋ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በአማራ ክልል በአዊ ዞን ዚገም ወረዳ ቅላዥ ከተማ፤ የመሰረተ ልማት ጥያቄ ያነሱ ነዋሪዎች በአደራ ፖሊስ ጣቢያ ያስቀመጧቸው የዞን አመራሮችና የፀጥታ ኃላፊዎች በመለቀቃቸው ግጭት ተፈጠሮ አራት ሰዎች ቆሰሉ። ነዋሪዎችና የዞን አመራር ያነጋገረችው ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።
ተጨማሪ ይጫኑ