በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤንሻንጉልና በኦሮሚያ በአምስት ቀናት ውስጥ 67 ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ


በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልልን የሚያሳይ የጎግል ካርታ
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልልን የሚያሳይ የጎግል ካርታ

ከሁለቱ ክልል ባገኘነው አጠቃላይ መረጃ በከተማው ውስጥ ከተገደሉት ሰዎች ጭምር በአምስት ቀናት ውስጥ የ67 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በቤንሻንጉል ጉምዝ ካማሼ ዞን በተለይ በበሎይ ጅጋንፎይ ወረዳ በተባባሰ ግጭት ከ72 ሺህ ሰዎች በላይ ተፈናቅለው ነቀምት እንደሚገኙ የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታከለ ቶሎሳ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

በደንብ የተደራጀና የታጠቀ ኃይል በተለይ ትላንት ከፍተኛ ጥቃት ከፍቶ በኦሮሚያ በኩል የሟቾች ቁጥር 23 መድረሱን ገልፀዋል።

የቤንሻንጉል ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አበራ ባይታ በበኩላቸው ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልፀው "ቁጥሩ የተጋነነ ነው" ብለውታል። በቤንሻንጉል ጉምዝ በኩልም 31 ሰዎች ሞተዋል ይላሉ።

በከተማው ውስጥ ዘጠኝ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጠዋል።

ከሁለቱ ክልል ባገኘነው አጠቃላይ መረጃ መጀመሪያ ላይ አራት ተገደሉ የተባሉ አመራሮችን ጨምሮ በአምስት ቀናት ውስጥ የ67 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች መኖራቸውና ብዙ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውና ሁለቱም ክልሎች ተናግረዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

በቤንሻንጉልና በኦሮሚያ በአምስት ቀናት ውስጥ 67 ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:16 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG